የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት የህግ ታራሚዎች ፍራሽና የህግ ታራሚዎች ደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

ማእከል ቤት ህንፀት ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰቲ ኣፋር
  • ጨረታዉ በኣዲዝ ዘመን ጋዜጣ የወጣበት ቀን:  7/2/2012
    ጨረታዉ የሚዘጋበት ቀን : ለተከታታይ 10 ቀናት ቀን ከረፋዱ 4:00  ሰዓት
    ጨረታዉ የመኪፈትበት ቀን : ለተከታታይ 10 ቀናት ቀን ከረፋዱ 9: 00 ሰዓት
  • ፍራሽ እና የደንብ ልብስ

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. በዚህ ግልጽ ጨረታ የሚወዳደሩ አቅራቢ ድርጅቶች በ2011 ዓ.ም በጀት አመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና ምዝገባ ሠርተፊኬት ማቅረብ አለበት፡፡
  2. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ሀሳብ ኦርጅናሉን በአንድ ፖስታ ኮፒውን በአንድ ፖስታ የተጫራቾቹ ስምና ፊርማ አድራሻ በግልፅ ተፅፎባቸው ሁለቱምፖስታዎችበአንድ ፖስታ ተደርጎ በሰም ታሽጎ መቅረብ ሲኖርበት ለሚግረቱት እቃዎች አይነት እና መጠን ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. የሚገዙት እቃዎችን አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (Specification) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  4.  ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው ከአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት በግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ደጋፊ ስራ ሂደት ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. የተዘጋጀው ጨረታ ዝርዝር ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ለተከታታይ 10 (አስር) ቀናት እስከ ከቀኑ 6፡00 ሰአት ድረስ ገዝተው በዛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰአት ተጫራቾች ባሉበት ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት በግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ደጋፊ ስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች ሰነዱን ገዝተው በመሙላት እና በማዘጋጀት ኦሪጅናል የመወዳደሪያ ሀሳብ ዶክመንታችሁን በአንድ ፖስታ ውስጥ በሰም በማሸግ ኮፒውን በሌላ ፖስታ ውስጥ በሰም በማሸግ በማስገባት ሁለቱንም ፖስታዎች በአንድ ፖስታ አድርጎ በሰም አሽገው ለዚሁ ግዥ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. ቢሮው ሊገዛው ያቀረበው የእቃ ዝርዝር ተጫራቹ ለሚሸጧቸው እቃዎች ስዕላዊ መግለጫ የሚያስፈልጋቸው ከሆነ በከለር የታተመ ስዕላዊ መግለጫ ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  8.  ሻጭ ንብረቱን በንብረት ክፍል ድረስ ወስዶ ካስረከቡ በኋላ በስሙ ሞዴል 19 አስቆርጦ ሂሳብ ክፍል በመውሰድ ሂሳቡን ማወራረድ አለበት፡፡
  9. አሸናፊው ድርጅት የአሸነፈበትን እቃዎች ወይም አገልግሎቶች በራሱ ትራንስፖርት ቢሮአችን ንብረት ክፍል ማስረከብ አለባቸው፡፡
  10. የጨረታው መክፈቻ ጊዜ እና ቀን የጨረታውን ፕሮግራም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን መክፈቻ ሂደት እያስተጓጉልም፡፡
  11. ቢሮው ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  12. ማንኛውም የጨረታ ተወዳዳሪ ለሚያቀርቧቸው እቃዎች ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ) የጨረታ ማስከበሪያ በCPO ከመወዳደሪያ ሃሳብ ማቅረቢያ ጋር በፖስታ ታሽጎ ማቅረብ አለበት፡፡

በተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለጎት በቢሮው ስልክ ቁጥር፡-033 -666-05-02 ደውለው ይጠይቁ፡፡

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ

መንግስት ማረሚያ ቤቶች

አስተዳደር ጽ/ቤት

ስፖንስርታትና

The ways ideas spread.
Milkta Logo