ትግራይ ልማት ማህበር ሓምሌ 29/1011 ዓ.ም ለሚያከብረው 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ለድምቀት የሚያግዙ የተለያዩ የሕትመት ስራዎች ለማሰራት ይፈልጋል

ማሕበር ልምዓት ትግራይ

1 ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ በሚገኘው ትግራይ ልማት ማህበር አዲስ ኣበባ ቦሌ መድሃኒ ኣለም ህድሞና ታወር 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 12 የማይመለስ ብር 100.00 እየከፈሉ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ::

2 ተጫራቾች በሚያቀርቡት ጨረታ ሰነድ ላይ ስም አድራሻ ስልክ ቁጥር እና ፊርማቸውና ማሕተም በግልፅ ማስፈር ይኖርባቸዋል::

3 ግልፅ ያልሆነ ወይም ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በጽሑፍ (በስልክ) በኣካል ማቅረብ ይችላል::

4 ተጫራቾች በሰንጠረዡ በተዘረዘሩትን ያንድ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በግልፅ መሙላት ይኖርባቸዋል:: ስርዝ ድልዝ ካለበት ጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማውን ያሳረፈ አካል መፈረም ይኖርበታል::

5 ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3,000 (ሶስት ሺ) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በድርጅቱ ስም በሲፒኦ ብቻ በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ኣንድ ላይ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::

6 ተጫራቾች በዘርፋ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ግብር የከፈለበት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number)፣ አግባብነት ያለው

የአቅራቢነት የምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::

7 ተጫራቾች አሸናፊ ሁነው ሲገኙ ስራውን በስንት ቀን ጨርሰው እንደሚያስረክቡ ባቀረቡት ዋጋ ዝርዝር መሰረት በግልፅ ማስቀመጥ ይጠበቅባችዋል፡፡

8 ተጫራቺች በቂ የሆነ፣ሕትመት መሳሪያዎች ያሏቸው መሆን አለባቸው፡፡

9 ፅ/ቤቱ ቅድያ ክፍያ (አድቫንስ)  አያስተናግድም ስራውን በትእዛዙ መሰረት ሰርተው ሲያስረክቡ ጥራቱ ተረጋግጦ የሚከፈለው  ይሆናል፡፡ ጥራቱን ተቀባይነት ያላገኘ ንብረቱ ተመላሽ ይደረጋል፡፡

10 ጨረታው ሐምሌ 10 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ አዲስ  አበባ ቦሌ መድሃኒኣለም ህድሞና ታወር 7ኛ ፎቅ በስም  በታሽገ ኢንቮሎፕ እጅ በእጅ ይዘው ሲቀርቡ ተጫራቾ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡

11  ከጽ/ቤቱ የዋጋ መስጫ ቅፅ ውጭ ዋጋውን ሞልቶ ማቅረብ ጨረታው ተቀባይነት የለውም፡፡

12 ማሕበራችን ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ እና ማህበሩን ሊጠቅም በሚችል መንገድ የማስኬድ  መብቱ  የተጠበቀ ነው፡፡

13 የሁሉም ስራዎች ዲዛይን በጽ/ቤቱ ተሰርቶ ስለሚቀርብላችሁ በምታቀርቡት ዋጋ  የዲዛይን ስራ ማካተት አይኖርባችሁም፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0116393852

ስፖንስርታትና

The ways ideas spread.
Milkta Logo