የመቀሌ ከተማ እቅድና ፋይናንስ ጽ/ቤት ለመቐሌ ከተማ ጽሕፈት ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቡልዶዘር እና ግሬደር፣ ጀነሬተር፣ አስፋልት /ሬንጅ/፣ ሰርቨር፣ የኢንተርኔት ዝርጋታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

ቤት ፅሕፈት ትልምን ፋይናንስን ከተማ መቐለ
  1. ቡልዶዘር እና ግሬደር
  2. ጀነሬተር
  3. አስፋልት /ሬንጅ/
  4. ሰርቨር
  5. የኢንተርኔት ዝርጋታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከታች የተዘረዘሩ መስፈርቶች የምታሟሉ ከጽ/ቤታችን ሰነድ ጨረታ በመውስድ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

ተፈላጊ መስፈርት፡-

1.  ማንኛውም በዘርፉ የተስማራና ብቃት ያለው የንግድ ድርጅት ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ለማቅረብ የሚችል መወዳደር ይችላል፡፡

2.  ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ከ22/4/2011 ዓ.ም ጀምሮ የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከመቀሌ ከተማ አግኣዚ ኦፕሬሽን ሕንፃ በሚገኘው የመቀሌ ከተማ እቅድና ፋይናንስ ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቁጥር 034 ማግኘት ይችላሉ፡፡

3.  ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ የዘመኑ ግብር የከፈሉበት የታደስ የንግድ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የቅርብ ወር ቫት ዲክላሬሽን የአቅራቢነት ምዝገባ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4.  ጨረታ ማስከበሪያ 1. ቡልዶዘር እና ግሬደር ብር 120,000.00 2. ጀነሬተር ብር 20,000.00 3. አስፋልት /ሬንጅ/ ብር 15,000.00 4. ሰርቨር ብር 15,000.00 የኢንተርኔት ዝርጋታ 120,000.00 በሲፒኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ በሁኔታ ያልተመስረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5.  ተጫራቾች የጨረታ ስነዳቸውን ለቴክኒካል አንድ አርጅናል እና ሁለት ኮፒ እንዲሁም ለፋይናንሻል ‹‹አንድ›› አርጅናል እና አንድ ‹‹ኮፒ›› በታሸገ ፖስታ ለየብቻቸው በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6.  ጨረታ የሚከፈትበት ቀን በ13/5/2011 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9፡00 ስዓትይከፈታል፡፡

7.  ተጫራቾች የመወዳደሪያ ስነዳቸው ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት አለባቸው።

8.  ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘብት ከላይ በተጠቀሰው ቀን በጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 034 ይከፈታል፡፡

9.  ተጫራቾች ስለጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር፦ 034 240 87 57/408501 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

10. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የመቀሌ ከተማ እቅድና ፋይናንስ ጽ/ቤት

ስፖንስርታትና

The ways ideas spread.
Milkta Logo