የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የትግራይ ክልል ጽ/ቤት Concentric service cable ባለ 6mm2 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

ሓይሊ መብራሕቲ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት አ/አ/ኤ/አ ጨንፈር ትግራይ ክልል

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር ት/ክ/ኤ/አ/004/2011

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የትግራይ ክልል ጽ/ቤት ከዚህ በታች በቀረበው ዝርዝር መሰረት Concentric service cable ባለ 6mm በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ቁጥር

የዕቃው ስምና ይዘት

መለኪያ

ተፈላጊ ብዛት

1

Concentric service cable ባለ 6mm2

ሜትር

800,000

1.የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበጀት ዓመቱ ለሚያከናውናቸው ተግባራት Concentric service cable ባለ 6mmእና ሌሎች  አክሰስሪዎች ግዢ ለማከናወን ባወጣው ግልጽ ጨረታ መሰረት ተወዳድረው የማምረት እና የቴክኒክ ብቃታቸውን በተቋሙ ኢንጂነሪንግ የጥራት ማረጋገጫ ሪሰርችና ዴቨሎፕመንት ዳይሬክቶሬት በኩል በመለየት Concentric service cable ባለ 6mm2 ለማምረት ብቁ መሆናቸው የተረጋገጠላቸው ድርጅቶች ሊወዳደሩ ይችላሉ፡፡

2. መስፈርቱን የሚያሟሉ በዘርፉ የተሰማሩ ብቃት ያላቸው የንግድ ድርጅቶችና መሳተፍ ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ የዘመኑን ግብር የተከፈለበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሊኖራቸው ይገባል፤

4. ተጫራቾች የመንግሥት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ዌብሳይት ላይ የተመዘገቡ መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።

5.  የተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 02 3ኛ ፎቅ በመምጣት የማይመለስ ብር 4,000.00/አራት ሺህ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውንና የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ከላይ በተጠቀሰው መሰረት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ (ሲፒኦ) ብር 240,000.00 /ሁለት መቶ አርባ ሺህ ብር/ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 7 ቀናት ከታች በተገለጸው አድራሻ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

7. አድራሻ፡- መቐለ ከተማ ፕላኔት ሆቴል አጠገብ የዛምራ ኮንስትራክሽን ሕንፃ ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የትግራይ ክልል ጽ/ቤት  3ኛ ፎቅ ፐሮኪዩርመንት ሎጂስቲክስ ዌር ሃውስ እና ፋሲሊቲ ቢሮ ቁጥር 01

8. ጨረታው የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ  ባሉት 7 ቀናት የመጨረሻ ቀን ከቀኑ 8፡30  ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀን ብሔራዊ በአል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ የሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ስዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡

9. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0342406712 መደወል ይችላሉ፡፡

10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የትግራይ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት

ስፖንስርታትና

The ways ideas spread.
Milkta Logo