የትግራይ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ የአይቲ ዕቃዎች (IT Equipment)፣ ኤሌክትሪክ ጀነሬተርና አነስተኛ የእጅ መሣሪያዎች፣ የእንሰሳት ሕክምና መገልገያ ዕቃዎች፣ የማንጎና የአቮካዶ ፍሬ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

ቢሮ ሕርሻን ገጠር ልምዓት ክልል ትግራይ

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር TG/AGP-CU

 10/2011

የትግራይ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ከግብርና ዕድገት ፕሮግራም (AGP-II) በተገኘ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ማለትም፡-

  • ሎት 1. የአይቲ ዕቃዎች (IT Equipments)
  • ሎት 2. ኤሌክትሪክ ጀነሬተርና አነስተኛ የእጅ መሣሪያዎች
  • ሎት 3.  የእንሰሳት ሕክምና መገልገያ ዕቃዎች
  • ሎት 4.  የማንጎና የአቮካዶ ፍሬ

በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑምበጨረታውላይለመሳተፍ  የምትፈልጉ  በዘርፉ  ሕጋዊ  ንግድ  ፈቃድ  ያላችሁ አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ እየጋበዝን የተዘጋጀው የጨረታ ዶክመንት ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብ/ በመክፈል ከታህሳስ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ከቢሮአችን የዕቃ ግዢ ንዑስ ሥራ ሂደት በሥራ ሰዓት እየመጣችሁ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን በጨረታዉ ላይ ለመሳተፍ ቀጥለዉ የተዘረዘሩትን ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡

  • የዘመኑ  የታደሰ የንግድ ፈቃድ የአቅራቢዎች ምዝገባ ሠርተፊኬት፣የቫት  ሰርተፈኬት፣ ያለፈዉ ወር ቫት ሪፖርት የተደረገበት ማስረጃ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ መመሪያውን በጥንቃቄ አይተው መወዳደርአለባቸው፡፡
  • የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በጨረታ ዶክመንቱ ላይ የተገለፀዉን መጠን በቢሯችን ስም በሲፒኦ አሠርተዉ ጨረታዉ ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ቢሮአችን በጨረታ ከቀረበው የዕቃዎች ብዛት እስከ 15% ለመቀነስ ወይም ለመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  • ጨረታው ታህሳስ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያዉ ዕለት በ4፡00 ሰዓት ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮአችን የዕቃ ግዥ ንኡስ ሥራ ሂደት ይከፈታል፡፡
  • ቢሮአችን የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች 0344-403663፣ 0344-404723 ወይም በፋክስ ቁጥር 0344-409971 መጠየቅ ይቻላል፡፡

የትግራይ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ 

ስፖንስርታትና

The ways ideas spread.
Milkta Logo