የትግራይ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ የመኪና ዘይትና ቅባት፣የእርሻ መገልገያ መሣሪያዎች፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የተሽከርካሪዎች መለዋወጫ ዕቃዎች፣የቢሮ ዕቃዎች/ፈርኒቸር/ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

የትግራይ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ

ጨረታ ቁጥር 10/2011

የትግራይ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ከዚህ በታች የተጠቀሱት የተለያየ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ማለትም፡-

  • ሎት 1. የመኪና ዘይትና ቅባት ለ2ኛ ጊዜ የወጣ
  • ሎት 2. የእርሻ መገልገያ መሣሪያዎች
  • ሎት 3.  የጽህፈት መሣሪያዎች
  • ሎት 4.  የተሽከርካሪዎች መለዋወጫ ዕቃዎች
  • ሎት 5.  የቢሮ ዕቃዎች/ፈርኒቸር/ ለ2ኛ ጊዜ የወጣ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታውለመሳተፍ  የምትፈልጉ  በዘርፉ  ሕጋዊ  የንግድ  ፈቃድ  ያላችሁ አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ እየጋበዝንየተዘጋጀው የጨረታዶክመንት ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100.00/ በመክፈል ሕጋዊ የንግድ ፈቃዳችሁን በመያዝ ከቢሮአችን የዕቃ ግዥክፍል ቢሮ ቁጥር 12 በሥራ ሰዓት እየመጣችሁ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በጩረታው ለመሳተፍ ቀጥለው የተዘረዘሩትን ማሟላትያስፈልጋል፡፡

  • የዘመኑ  የታደሰ ንግድ ፈቃድ አቅራቢዎች ምዝገባ ሠርተፊኬት፣የቫት  ሰርተፈኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) እና ያለፈውወር  ቫት ዲክለር የተደረገበት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መቅረብ አለበት፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ መመሪያውን በጥንቃቄ አይተው መወዳደርአለባቸው፡፡
  • የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በጨረታ ዶክመንቱ ላይ የተጠቀሰው መጠን ገንዘብ በሲፒኦ  አሠርተው ጨረታው ከመከፈቱበፊትአያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ቢሮአችን በጨረታ ከቀረበው የዕቃዎች ብዛት እሰከ 20% የመጨመርወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ጨረታው ታህሳስ 4 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያውኑ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮአችን የዕቃ ግዥ ክፍል ይከፈታል፡፡
  • ቢሮአችን የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች 0344403663/0344404346 ወይም በፋክስ ቁጥር 0344409971 /0344403663 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ስፖንስርታትና

The ways ideas spread.
Milkta Logo