ግልፅ የጨረታ ማሰታወቂያ
የወልቃይት ስኮር ልማት በ 2006/2007 የምርት ዘምን በራሱ ማሳ ላይ ያመረተዉን ከ 30000 እስከ 3300ኩንታል የሚገነት ጥጥ ከወልቃይት ወደ ዳንሻ ለማጎጎዝ በደረቅ ጭነት ትራንስፖርት የተሰማሩ ህጋዊ ነጋዴዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማስራት ስለሚፈልግ መስፈርቱን የምታሞሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ይጋብዘል ::
-
ህጋዊ የታደሰ አዲስ የንግድ ስራ ፈቃደ : የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት/TIN/ እና በመንግስት የአቅራቢዎች ዝርዝር ዉስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
-
ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል መቀሌ ከተማ ሃወልት ሰማእታት መንገድ ዓዲ ሐዉሲ መገንጠያ ድልድል አከባቢ የድሮ ጋዜጣ ወይን ቢሮ የነበረ ህንፃ ከሚገገኘዉ የፕሮጀክቱ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት /ላይዘን ኦፊስ / አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 04 ወይም የወልቃይት ስኮር ልማት ፕሮጀክት ዋና መስራቤት የፋይናንስ : አቅርቦትና ፋሲሊቲ ዘርፍየጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላሉ::
-
ጨረታዉ በአየር የሚቆይበት ግዜ ከታህሳስ 05 /2007 ዓ/ም እስከ ታሀሳስ 19/2007 ዓ/ም ሲሆን የጨረታ ሳጥን የሚዘጋበት ከታህሳስ 20/2007 ዓ/ም ከጥዋቱ 3:00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ 3:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል::
-
የጨረታ ሰነድ ገቢ የሚደረግበትና የሚከፈትበት ቦታ መቀሌ የሚገኝ የፕሮጀክቱ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ይከፈታል
/ላይዘን ኦፊስ/ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 04 ይሆናል::
-
ፕሮጀክቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::
ለተጨማሪ መብራርያ በስልክ ቁጥር መቀሌ ላይዘን ኦፊስ 0344416552 ሞባይል ቁጥር 0914780705
ወልቃይት ስኮር ልማት ፕሮጀክት 0345592072 ሞባይል ቁጥር 0910520195/ 0914780988 መጠየቅ ይቻላል::