ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው
እድትሳተፉ ይጋብዛል::
1. በዚህ የስራ መስክ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር
የከፈሉ መሆን አለባቸው (የማስረጃው ፎቶ ኮፒ ማያያዝ ያስፈልጋል)
2. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ የጨረታ ዋጋ ሲያስገቡ በጨረታ ስነዱ
በተገለፀው ስፔስፊኬሽን መሆን አለበት፣ከስፔስፊኬሽን ውጭ ያቀረበ
ተቀባይነት አይኖረውም፣
3. ተጫራቶች የጨረታ ዋጋቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚጨምርና
የማይጨምር መሆኑ በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው፣ካልገለፁ የጨረታ
ዋጋው የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዳካተተ ይቆጠራል::
4. የጨረታው አሸናፊ ጨረታው አሽናፊ መሆኑ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ
ያሸነፋቸው ዕቃዎች በ20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ መቀሌ በሚገኘው
ስቶራችን ድረስ በራሱ ትራንስፖርት በማጓጓዝ ማስረከብ አለበት::
5. ተጫራቾች ላሽነፉበት ገንዘብ ክፍያ የሚፈፀምላቸው ያሽነፉት ዕቃ
ኢንስፔክት ተደርጎ የገቢ ደረስኝ ከተቆረጠለት በኃላ መሆኑ ተጫራቾች
አስቀድመው ማወቅ አለባቸው::
6. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50 /አምሳ ብር/
በመክፈል ከመቀሌ ዋና መ/ቤት ከግዢ፣ንብረት አቅርቦትና ቁጥጥር
መምሪያ ቢሮ ወይም ከአዲስ አበባ ላይዘን ኦፊስ ግዢ ማስተባበሪያ
በድሉ ሕንፃ በስራ ስዓት መውሰድ ይችላሉ፣
7. የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ያስገቡት ዋጋ 2% በትራንስ ኢትዮጵያ
ኃ.የተ.የግ ማህበር ሰም በሲፕኦ (CPO) መልክ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
ሲፒኦ ያላስያዘ ተጫራች ወድያው ከጨረታ ይሰረዛል፣
8. ተጫራቾች በተሰጣቸው ሰነድ ውስጥ ብቻ ዋጋቸውን ሞልተው በሰም
በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ጥር 13 ቀን 2009 ዓ.ም ከጥዋቱ 4፡00
ባለው ጊዜ ውስጥ በአዲስ አበባ ላይዘን ኦፊስ ግዢ ማስተባበሪያ በድሉ
ሕንፃ ወይም መቀሌ በሚገኘው የግዢ፣ ንብረት አቅርቦትና ቁጥጥር
መምሪያ ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ
ማስገባት አለባቸው::
9. በጨረታ ሰነዱ የተቀመጠ ቁጥርም በPO ጊዜ ሊጨምር ወይም
ሊቀንስ ይችላል፣
ጨረታው በዚሁ ቀን ማለትም ጥር 13 ቀን 2009 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30
ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመቀሌ ዋና
መ/ቤት በትንሿ አደራሽ እና በአዲስ አበባ ላይዘን ኦፊስ ግዢ ማስተባበሪያ
ቢሮ በድሉ ሕንፃ በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል:: በዕለቱ ተጫራቾች
ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታ ሰነዱ ከተሟላ ይከፈታል::
10. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ
በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ተጨማሪ ማብራርያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 034-441 64 39 / 034-440 82 05 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::