የብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፡-ራዩ/ግአስአ/ግጨ-001/2017
ራያ ዩኒቨርስቲ ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተመለከቱትን ምድብ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ምድብ | የእቃው አገልግሎት ዓይነት | የሰነድ መግዣ ዋጋ | የጨ/ማ ዋስትና መጠን | የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ዓይነት | ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት | ጨረታው የሚዘጋበት ቀን | ጨረታ የሚከፈትበት ቀን | |||
ቀን | ሰዓት | ቀን | ሰዓት | ቀን | ሰዓት | |||||
ምድብ 01 | ዳቦ | 500 | 50,000.00 | ጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንከ የሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በህጋዊ ባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክረዲት | ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን | 11:00 | በ16ኛው ቀን | 4:00 | በ16ኛው ቀን | 4:30 |
ምድብ 02 | የተማሪዎች የምግብ ግብአት የሆኑ የፋብሪካ ውጤቶች | 500 | 30,000.00 | ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን | 11:00 | በ16ኛው ቀን | 4:00 | በ16ኛው ቀን | 4:30 | |
ምድብ 03 | የተፈጨ በርበሬ | 500 | 10,000.00 | ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን | 11:00 | በ16ኛው ቀን | 4:00 | በ16ኛው ቀን | 4:30 | |
ምድብ 04 | የተማሪዎች ሎከር እና ወንበር | 500 | 30,000.00 | ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን | 11:00 | በ16ኛው ቀን | 4:00 | በ16ኛው ቀን | 4:30 |
ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት እና ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዮችን በጨረታ ሰነዱ ላይ በመመልከት እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።
1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ የምዝገባ ሰርተፊኬት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል (ጊዜ ገደቡ ያላለፈበት) ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሚሰጥ ታክስ ክሊራንስ፣ ጨረታ ማስከበርያ ዋስትና፣ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ EGP የተመዘገበ ወይም የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ማስረጃ፣ ሌሎች ዝርዝር የቴከኒክ መመዘኛዎች እንደየ ምድቡ ስለሚለያዩ በጨረታ ሰነዱ ላይ ይመልከቱ።
2. የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ምድብ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛውቀን 11፡00 ሰዓት ብቻ ራያ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ ህንፃ ቁጥር 5፡ ምድር ቤት /ግራውንድ/ በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
3. ከዋናው የጨረታ ሰነድ የሚያስፈልጉ የኮፒዎች ብዛት 1 ሲሆን በአጠቃላይ በ2 የተለያዩ ፖስታዎች ማለትም ዋና/ኦሪጅናል የሚል ምልክት ያለው የነዚሁ ሁሉም ሰነዶች ኮፒ ደግሞ በሌላ ፖስታ ቅጂ/ኮፒ የሚል ምልክት በማይለቅ ቀለም ተፅፎ ለየብቻው ታሽጎ የጨረታ ሳጥኑ ከመዘጋቱ በፊት በግዥ አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ ህንፃ ቁጥር 5 ግዥ ቡድን ምድር ቤት /ግራውንድ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
4. ጨረታ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 በተራ ቁጥር 2 በተገለፀው አድራሻ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
5. ተጫራቾች አሸናፊ ለሆኑባቸው እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ዩኒቨርሲቲው ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
6. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 034 877 0501