መሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ሃ/የተ/የግ/ማ
ለምርት አገልገሎት Raw Pet coke imported አወዳድሮ ለመግዛት የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቅያ ቁጥር 45/2016
ክፍል አንድ
- መሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ለምርት አገልግሎት የሚጠየቀው 45,000 ሜትሪክ ቶን Raw pet coke imported አቅራቢዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- በጨረታው የሚሳተፉ ድርጅቶች Import & Export በዘርፉ የተሰማሩ መሆናቸው የሚገልፅ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸው፣ የሚገልፅ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ኣያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺ ብር) በመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ሃ/የተ/የግ/ማ ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (cpo) ወይም ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒካል ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከላይ በተራ ቁጥር 2 ከተጠቀሱት ማስረጃዎች ጋር በማያያዝ የድርጅታቸውን ኣርማና ማህተም ያለው ደብዳቤ በመፃፍ ለጨረታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከዚህ ግልፅ ጨረታ ማስታወቅያ ጋር ኣብሮ ከተገለፀው ዝርዝር መግለጫ መሰረት ያቀርቡትን Raw pet-coke imported በጨረታው ቀን ወይ ከዛ በፊት በራሳቸው ወጪ ለምርመራ ናሙና (ሳምፕል) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።(ናሙናው የሚቀርበው መቀሌ በሚገኘው ዋና ፋብሪካ ይሆናል)
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረብያቸውና በተራ ቁጥር 2 እና 3 ላይ የተጠቀሱት ሰነዶችና በተራ ቁጥር 5 የተጠቀሰውን ናሙና (ሳምፕል) እስከ ሰኔ 15/10/2016 ከጠዋቱ 4፡00 ሰኣት ድረስ በታሸገ ኢንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸው መቀሌ በሚገኘው የፋብሪካው ዋና መስሪያ ቤት 3ኛ ፎቅ ቁጥር 15 ስለሚገኝ የግዥና አቅርቦት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በእለቱ 15/10/2016 ከጠዋቱ 4፡15 ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 4፡15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ፋብሪካው ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
መሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ሃ/የተ/የግ/ማ
ስልክ +251 34 241 0085/+251 34 440 5806
ሞባይል +251 912 502 596
ፋስክ+251 34 441 0863
E-mail: procurementmessebocement2020@gmail.com
መቐለ