በትግራይ ክልል ትግራይ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ ግዥና ንብረት ኣሰተዳደር ለ2016 በጀት አመት የብሮድካስትና ተዛማጅ እቃዎች በሀገር ኣቀፍ ደረጃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ኤጀንሲ መራከቢ ሓፋሽ ትግራይ

በትግራይ ክልል ትግራይ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ ግዥና ንብረት ኣሰተዳደር ለ2016 በጀት አመት የብሮድካስትና ተዛማጅ እቃዎች በሀገር ኣቀፍ ደረጃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ኣለባቸው።

➢ የ2016 ዓ/ም ህድሳት የተደረገለት ንግድ ፍቃድ፡የኣቅራቢነት ምዝገባ ሰርቲፊኬት የቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት የጥቅምት ወር የቫት ዲክላሬሽን ቲን ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ ኣለባቸው

➢ መስፈርቶቹን የሚያሟሉ ሁሉም ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 (ኣስራ አምስት ) ቀናት ውስጥ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነድ ከትግራይ መገነኛ ብዙኃን ኤጀንሲ ግዥና ንብረት ኣሰተዳደር ቢሮ ቁጥር 106 ከቀን 09/05/2016 ዓ/ምእስከ 23/05/25016 ዓ/ም ከቀኑ 11:30 ድረስ በስራ ሰአት ሰነዶችን መግዛት ትችላላቹ ።

➢ ጨረታው የሚዘጋበት የመጨረሻ ቀን 24/05/2016ዓ/ም ከጥዋቱ 4:00 ሰኣት ላይ ተዘግቶ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን 24/05/2016ዓ/ም ጥዋት 4:30 ቢሮ ቁጥር 106 ይከፈታል።

➢ የጨረታማስከበርያ ዋስትና/ በተጫራቶች ምርጫ ከሚከተሉት ዓይነቶች አንዱ ሊሆን ይችላል።

ሀ. በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና፤

ለ. በማይሻር ሌተር ኦፍ ክሬዲት የተረበ ዋስትና፤

ሐ. በአገር ውስጥ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የክፍያ ትዕዛዝ ሁኖ 130,000.00(አንድ መቶ ሰላሳ ሺ ብር) ማስያዝ ኣለባቸው።

➢ የሚያሰፈልጉት የደኩመንት ብዛት ቴክኒካል ኦርጅናል ደኩመንትና ኮፒ፣ ፋይናንሻል ኦርጅናል ደኩመንትና ኮፒ ለየብቻቸዉ በፖስታ በማሸግ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸዉ ።

➢ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ያሉትን ቅፆች በትክክል በመሙላት፣ በያንዳንዱ የሰነዱ ቅፅ ፈርማ እና የድርጅቱ ማሕተም ማድረግ ኣለባቸው።

➢ ድርጅታችን ትግራይ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ ይህ ጨረታ በማንኛውም ግዜ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኣድራሻ-ትግራይ መቐለ
ትግራይ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ
ቢሮ ቁጥር ----106 ግዥና ንብረት ኣስተዳደር
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር ውይ ዕድ 0342406380 ፋክስ ቁጥር 2510344402860

ስፖንስርታትና

The ways ideas spread.
Milkta Logo