ትግራይ የጦር ጉዳቶኞች ማህበር ከ2013 ዓ.ም. እስከ 2015 ዓ.ም. የሶስት አመት የገንዘብና ንብረት እንቅስቃሴ በውጭ ኦዲተር (External Auditor) ማስመርመር (ኦዲት) ማስደረግ ይፈልጋል

ማሕበር ተጋደልቲ ትግራይ

የሒሳብ ምርመራ ጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ትግራይ የጦር ጉዳቶኞች ማህበር ከ2013 ዓ/ም እስከ 2015ዓ/ም የሶስት ኣመት የገንዘብና ንብረት እንቅስቃሴ በዉጭ ኦዲተር /external auditor/ ማስመርመር/ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶች እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

  1. በኦዲተርነት ሙያ ህጋዊ የስራ ፍቃድ ያለው ሁኖ የ2015 ዓ.ም የታደሰ ፍቃድና የዘመኑ ግብር የከፈለ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ ማቅረብ የሚችል።
  2. ከዚህ በፊት በዚህ ስራ መስራቱን የሚያረጋግጥ ከ2 ድርጅቶች የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል።
  3. ለጨረታ ማስከበርያ ብር 6,000.00 (ብር ስድስት ሺህ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በድርጅታችን ስም የተዘጋጀው በባንክ የተረጋገጠ ቼh /C.P.O/ ማቅረብ አለበት።
  4. ከላይ የተዘረዘሩት መስፈርቶች የምታማሉ ተወዳዳሪዎች የምትጫረቱበትን ዋጋ TIN ቁጥርና ህጋዊ ንግድ ፍቃድ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቅያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
  5. ጨረታው በ15ኛው ቀን በ9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ10፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማህበሩ ዋና ጽ/ቤት መቐሌ ከተማ ይከፈታል። 15ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል።
  6. አሸናፊው ተጫራች ውል ሲፈርም የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋ 10% (አስር በመቶ) በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ የማስያዝ ግዴታ አለበት።
  7. የጨረታው አሸናፊ መሆኑ በፅሁፍ ወይም በቃል ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በተካታታይ 7 ቀናት ውስጥ ውል በማሰር የምርመራ ሪፖርት ውል ከተፈረመ ቀን ጀምሮ በ30 ተከታታይ የሰራ ቀናት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 በመክፈል ይህ ማስታወቅያ በኣዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱ በመቐለ ይሓ ሪል እስቴት ሰንተር ቁጥር2 6ኛ ፎቅ ወይም በአዲስ አባበ መስተባበርያ ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  9. ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም

አድራሻ፦ መቐሌ ዋና ጽህፈት ቤት

* አዲስ አበባ ማስተባበርያ ቢሮ ጊዮን ሆቴል አከባቢ

ሞባይል 0914 70 08 69/ 0943 65 54 00

ስልክ ቁጥር 034 441 3646/ 0966 93 01 89/011 553 6699

ማሕበር ጉዱኣት ኩናት ትግራይ

ስፖንስርታትና

The ways ideas spread.
Milkta Logo