የመቀሌ ከተማ እቅድና ፋይናንስ ፅ/ቤት ለተለያዩ ፅ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ የፅህፈት መሳሪዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

ቤት ፅሕፈት ትልምን ፋይናንስን ከተማ መቐለ

የጨረታ ማስታወቂያ

የመቀሌ ከተማ እቅድና ፋይናንስ ፅ/ቤት ለተለያዩ ፅ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ የፅህፈት መሳሪዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

በዚሁ መሰረት የሚቀጥሉ መስፈርት የሚያማሉ መወዳደር ይችላሉ::

1 ማንኛዉም በዘርፉ የተሰማራና ብቃት ያለዉ የንግድ ድርጅት ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ለማቅረብ የሚችል መወዳደር ይችላል::

2 ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ከ 26/12/ 2006 ዓ/ም ጀምሮ የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ/ ብር በመክፈል ከዚህ በታች ከተጠቀሱት አድራሻዎቻችን ማግኘት ይችላሉ::

በኣግአዚ ኦፕሬሽን በሚገኘዉ የመቀሌ ከተማ እቅድና ፋይናንስ ፅ/ቤት ( 1 ፎቅ ቁጥር 034)

3 የጨረታ ሰነዶችን ጨረታዉ ሬድዩ ፋና ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ከታች በተገለፀዉ ኣድራሻችን በመቅረብ ማግኘት ይቻላል::

4 ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ የንግድ ፍቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የአቅራቢነት መለያ ካርድ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ( Tin Number) ምስክር ወረቀት ማቅለብ የሚችሉ::

5 ተጫራቾች ፅ/ቤቱ ያቀረበዉ ናሙና ማየት ይኖርባቸዋል ::

6 ተጫራቾች ለፅህፈት መሳሪያ ብር 16.000 (ኣስራ ስድስት ሺ ብር ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል ::

7 ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸዉን በሁለት ፖስታ ”” ኣንድ ኦርጅናል’’ እና አንድ ‘ኮፒ ‘ በሰም በታሸጉ ኢንቨሎፖች እስከ ቀነ 13/01/2007 ዓ/ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት በፊት ከላይ በተጠቀሰዉ የፅ/ቤቱ ኣድራሻ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸዉ::

8 ጨረታ በተመሳሳይ ቀነ 13/01/2007 ዓ/ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በፅቤቱ ቢሮ ቁጥር 034 ይከፈታል በተጨማሪም ተጫራቾች ስለ ጨረታዉ ማብራሪያ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር 0344406839 /408501 በተጠቀሰዉ ኣድራሻ ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ::

9 ይህ ጨረታ የሚቆይበት ጊዜ ( Validity period) ጨረታዉ ከተከፈተ ቀነ ጀምሮ ቢያንስ ለ 45 የስራ ቀናት የፀና ይሆናል::

10 ፅ/ ቤቱ የተሻለ ኣማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ

የመቀሌ ከተማ እቅድና ፋይናንስ ፅቤት ( 1 ፎቅ ቁጥር 034)

 

ስፖንስርታትና

The ways ideas spread.
Milkta Logo