የኣላማጣ ከተማ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ለተለያዩ ፕሮግራም ኣገልግሎት የሚሆን ትልቁ ነጭ ድንኳን (White big curve stand tent/8m*20 m ለመግዛት በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኝ ሲሆን በግልፅ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል።

የኣላማጣ ከተማ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት

1 በስራ መስኩ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ኮፒ

2 የቫት ሰርተፊኬት ኮፒ እና የመጨረሻዉ ወር ቫት ሪፖርት ኮፒ

3 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ኮፒ

4 የታደሰ የኣቅራቢነት ሰርተፊኬት ኮፒ

5 ኣንዱ በሰጠዉ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ኣይፈቀድም።

6 የዋጋ ማቅረቢያ በድርጅታቸዉ የጨረታ ማቅረቢያ ሰነድ ይሆናል።

7 የጨረታዉ ሰነድ ፋናንሻል እና ስፒኦ በተለያየ ፖስታ የሚያቀርብ ሁኖ ኣብሮ መታሸግ ይገባዋል።

8 የኤሌክትሮኒክስ ጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ማህተም እና ፊርማ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

9 በኤሌክትሮኒክስ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች በቀረበው ዝርዝር ስፔስፊኬሽን መሰረት የሚያቀርቡትን ኣይነት ንብረት ዝርዝር ቴክኒካል መግለጫ በግልፅ በመዘርዘር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

10 የሚያፈቀርቡትን ዋጋ 15% ቫት (የተጨማሪ እሴት ታክስ) ያካተተ መሆን ኣለበት፤

11 በጨረታው ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን ስም፣ ሙሉ ኣድራሻ፣ በባለቤትነት ወይም በህጋዊ ውክልና ባለው ግለሰብ ፊርማቸው እና የድርጅታቸውን ማህተም በግልፅ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል። ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።

12 የጨረታዉ ሰነዱን ከሕዳር 27/2011 ዓ/ም እስከ ታሕሳስ 07/2011 ዓ/ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2:30 እስክ 6:00 እና ከሰኣት በኃላ ከ 8:30 እስክ 11:00 ድረስ በትግራይ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት መቀሌ ኣክሱም ሆቴል ኣጠገብ በኣካል በመቅረብ ብር 50.00 ብቻ በመክፈል ሰነድ መግዛት ይቻላል።

13 ተጫራቾች ያዘጋጀቱን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጥዋቱ 2:30 እስክ 6:00 እና ከሥኣት በሃላ ከ 8:30 እስክ 11:00 ድረስ በትግራይና ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት መቀሌ ኣክሱም ሆቴል ኣጠገብ በኣካል በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

14 የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ታሕሳስ 8/2011 ዓም ከጥዋቱ 3:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባለመገኘት ሳይከፈት የሚቀር የጨረታ ሰነድ ኣይኖርም።

15 ምክርቤታችን ኣስፈላጊ ሁኖ ካገኘዉ የጨረታዉን መክፈቻ ቀን በግልፅ ኣሳዉቆ ማራዘም ወይም ያላምንም ቅድመ ሁኔታ ጨረታዉን በከፊል ወይም በመሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነዉ።

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo