የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ECC/MB/NCB 001/2017
የኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮምሽን የመቐለ ቅ/ፅ/ቤት ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የሚከተሉትን አገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
- ሎት አንድ የሰራተኞች የጧትና ከሰዓት ሰርቪስ አገልግሎት መኪና ኪራይ ግዥ ፣
- ሎት ሁለት የሙሉ ቀን ሰርቪስ አገልግሎት መኪና ኪራይ ግዥ፣
- ሎት ሶስት ባለ ግማሽ ሊትር እሽግ ውሃ አቅርቦት ግዥ፣
- ሎት አራት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል በቦቴ የውሃ አቅርቦት መኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ፣
- ሎት አምስት ባለ 3 ኮኮብ የሆቴል አገልግሎት ግዢ፣
- ሎት ስድስት ባለ 4 ኮኮብ የሆቴል አገልግሎት ግዢ፣
- ሎት ሰባት በባለ ባህላዊ የምግብ አዳራሽ የሆቴል አገልግሎት ግዢ፣
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. በሁሉም ሎቶች ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
2. የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ወይም በትግራይ ክልል እቅድና ፋይናንስ የአቅራቢነት ፈቃድ ውስጥ የተካተቱ መሆን ይኖርባችዋል።
3 . ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ።
4.ተጫራቾች ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. የጨረታ ማስከበሪያ በሁሉም ሎቶች ብር 50,000.00 ለእያንዳንዳቸው በባንከ በተመሰከረለት ቼክ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ።
6. በሎት አምስትና ስድስት ለሚሳተፉት በያንዳንዳቸው በተገለፀው ኮከብ በደረጃ መዳቢ የተረጋገጠና በፌደራል ወይም በትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የተመዘገበ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ አለበት።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቅያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መከፈቻ ቀን ድረስ ትራንስ ኢትዮጵያ አጠገብ የሚገኘው የጉምሩከ ኮምሽን መቐለ ቅርንጫፍ የግዥና ፋይናንስ ቡድን ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢቨሎፕ በማድረግ ነሃሴ 21/2016 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታውም በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 በመስሪያ ቤቱ ሃብት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 301 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
9. የጨረታው አሸናፊ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና 10 /አስር በመቶ/ CPO በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ከሎት አንድ እስከ አራት ያሉት ለሶስት ዓመታት እንዲሁም ከሎት አምስት እስከ ሰባት ያሉት ለአንድ ዓመት ውል ይፈራረማል።
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማረጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 0342-40-71-62/09 19 068 385/09 14 830 469
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮምሽን የመቐለ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት