የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ የመድን ካሳ ክፍሉ የተረከባቸውን፡- ቀረጥ የተከፈለባቸው ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች • ልዩ ልዩ የተሸከርካሪ ውጫዊና የውስጥ አካላት • የተለያዩ ብረታ ብረቶችን በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል ማንኛውም የስም ማዛወሪያ ተጨማሪ የጉምሩክ ቀረጥ፣ግብር፣እሴት ታክስና ሌሎች ወጪዎች ቢኖሩ ከፍሎ ለመግዛት የሚፈልግ

የኢትዩያ መድን ድርጅት

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ የመድን ካሳ ክፍሉ የተረከባቸውን፡-

• ቀረጥ የተከፈለባቸው ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች

• ልዩ ልዩ የተሸከርካሪ ውጫዊና የውስጥ አካላት

• የተለያዩ ብረታ ብረቶችን በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል

ማንኛውም የስም ማዛወሪያ ተጨማሪ የጉምሩክ ቀረጥ፣ግብር፣እሴት ታክስና ሌሎች ወጪዎች ቢኖሩ ከፍሎ ለመግዛት የሚፈልግ ሁሉ ቃሊቲ ክራዉን ሆቴል በስተጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል በመገኘት ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 21 ቀን 2016 ድረስ በመመልከትና የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ መድን ድርጅት /Ethiopian |nsurance Corporation/ስም በተሰራ ሲፒኦ በማስያዝ መጫረት ይችላል፡፡

በተጨማሪም የጨረታ መነሻው ብር 125,000 የሆነ እና የሰሌዳ ቁጥሩ 3-59470 ኢት ሲኖ ገልባጭ ተሽከራካሪ በትግራይ ክልል ክልተ አውላዕሎ ወረዳ ልዩ ስሙ እንዳአብርሃ ወአፅበሃ አከባቢ ገደል ውስጥ ተገልብጦ የሚገኝ ሲሆን በመለዋወጫነት በጨረታ ስለሚሸጥ ተጫራቶች በቦታው ተገኝታችሁ መመልከት ትችላላችሁ፡፡

ለበለጠ መረጃ ፡ መቐለ ዲስትሪክት ስልክ ቁጥር 0344-4052-75/ 0911-9587-37 መደወል ይቻላል፡፡

ሀ/ የዕቃ ማስያዣ፡- የጨረታ መነሻ ዋጋ 20 በመቶ ሲሆን ዝቅተኛ የዕቃ ማስያዣ ብር 1000 ነው፡፡

ለ/ የተሸከርካሪ ማስያዣ

የጨረታ መነሻእስከ ብር 50,000.0020 በመቶ
ከብር 50,001.00እስከ ብር 100,000.00ብር 15,000.00
ከብር 100,001.00እስከ ብር 200.000.00ብር 25,000.00
ከብር 200,001.00እስከ ብር 300,000.00ብር 37,000.00
ከብር 300,00100እስከ ብር 400,000.00ብር 50,000.00
ከብር 400,001.00እስከ ብር 500,000.00ብር 60,000.00
ከብር 500,001.00እስከ ብር 800,000.00ብር 75,000.00
ከብር 800.001.00ብር በላይብር 100,000.00

ተጫራቶች የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት በመሙላት የጨረታውን ሠነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ/ም ከጥዋቱ 2.30 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10.00 ሰዓት ድረስ ለገሀር በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታዉ ግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ/ም ከጥዋቱ 3:00 ሰዓት ቃሊቲ በሚገኘው በሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል ይከፈታል፡፡ በጨረታዉ ተሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታዉ ከተከፈተበት ቀን ከሁለት የስራ ቀናት በኃላ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን ሂሳቡ በገዙት ንብረት ላይ የሚታሰብ ሆኖ የገዙትን ንብረት ተጫራቶች መክፈል ከጀመሩበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ጊዜ ውስጥ ክፍያ አጠናቀው ንብረቱን ባይረከቡ ለጨረታ ተሳትፎ ያስያዙት ገንዘብ በመቀጫ መልክ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታዉ ይሰረዛል፡፡ ክፍያ ፈፅመው ንብረቶቹን በተገለፀው ጊዜ የማያነሱ ተጫራቶች የጥበቃ ወጪ በቀን ብር 150.00/አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ ይከፍላሉ፡፡

ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ያሸነፈውን ተሽከርካሪ ሆነ ቁሳቁስ በአለበትሁኔታ በአንድ ጊዜ ማንሳት አለበት፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 011-439-25-89 እና 011-439-25-45መጠየቅ ይችላል፡

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo