ራያ አግሮ ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር በትግራይ ደቡባዊ ዞን በአላማጣ ከተማ ለሚያቋቁመው የወተት ማቀነባበርያ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል የቢሮ እና የሕንፃ ግንባታ ዲዛይን ማሠራት በማስፈለጉ በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የተሰማሩ ባለሙያዎችን በጨረታ በማወዳደር ማሠራት ይፈልጋል

ራያ አግሮ ኢንዱስትሪ ኣክሲዩን ማህበር
  1. ጨረታዉ በኣዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣበት ቀን: 25/12/2012
    ጨረታዉ የሚዘጋበት ቀን: 16ኛዉ ቀን 4:00 ሰዓት
    ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን : በ16ኛዉ ቀን 4:30 ሰዓት ይከፈታል ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ከጥዋቱ 400 ሰዓት ታሽጎ 4:30 ላይ ይከፈታል
  2. በዘርፉ እና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ፣
  3. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር / TIN/ ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  6. ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተሰጠና የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
  7. በተቀመጠው ጊዜ በፕሮጀክት ስፍራ በመሄድ አስፈላጊውን መረጃ በመውሰድ ዲዛይን ማድረግ የሚችሉ፣
  8.  በወተት ማቀነባበርያ የግንባታ ዲዛይን ሥራና በተዛማጅ ሥራዎች የሠሩ ከሆነ ተመራጭ ነው፡፡
  9. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተቁ፡ 1-7 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
  10. ዲዛይን የሚደረገው ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፣
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን 2% /አንድ ፐርሰንት/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  12. ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሠነድ መገናኛ ደራርቱ ቱሉ ሕንፃ 9ኛ ፎቅ ቢ.ቁ 02 የማይመለስ ብር 100.00/ አንድ መቶ ብር/ ብቻ ከፍሎ መውሰድ ይችላል፡፡
  13. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዳቸውን ሞልተው በኤንቨሎፕ ላይ ስማቸውንና ስልክ ቁጥር በመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  14. በጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከሉ ቢሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜና ዕሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ውድድሩን በሎት ወይም በተናጠል ሁለቱንም አማራጭ የመጠቀም መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው መረጃ ከፈለጉ ማዕከሉ ድረስ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር፡- 0983027322/0911421954 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሰመሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ራያ አግሮ ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo