የሰሜን ሪጅን የመ/ሠ/ማ/ዋ/ኤጀንሲ እና በስሩ ለሚተዳደሩት ቅ/ጽ/ቤቶች ለ2012 ዓመት አገልግሎት የሚውሉ፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፣ ቋሚ ንብረቶች ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ ሸልፍ፣ የደንብ ልብስ፣ ጫማ፣የመኪና ባትሪዎች፣ የሞተር እና የመሪ ዘይት ወዘተ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

በኢፌዲሪ በግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ሰሜነ ሪጅን ፅ/ቤት
  • የጽህፈት መሳሪያዎች፣
  • አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፣
  • ቋሚ ንብረቶች ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ ሸልፍ፣
  • የደንብ ልብስ፣ ጫማ፣
  • የመኪና ባትሪዎች፣
  • የሞተር እና የመሪ ዘይት ወዘተ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቶች፣ 
  1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ 
  2. በገንዘብ ሚ/ር በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እንዲሁም የ2012 ዓ.ም ጨረታ መሳተፍ የሚችሉ ለመሆናቸው; ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ አካል የተሰጣቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ። 
  3. ከአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ውስጥ በተለያዩ ጥፋቶች ያልተሰረዙ ወይም የቅጣት ጊዜያቸውን ያላጠናቀቁ በዚህ ጨረታ መሳተፍ አይችሉም። 
  4. እያንዳንዱ ተጫራች በተራ ቁጥር 1ኛ ለተገለጸው የጽሕፈት መሳሪዎች፣ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች ቋሚ ንብረቶች ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ ሸልፍ የደንብ ልብስ፣ ጫማ ፣ የመኪና ባትሪዎች፣ የሞተር እና የመሪ ዘይት ወዘተ ጨረታ ብር 3000.00 (ሦስት ሺ ብር) የጨረታ ማስከበርያ ሲፒኦ (ጥሬ ገንዘብ) በጽ/ቤቱ ስም ማቅረብ ይኖርበታል። 
  5. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በሂሳብ ክፍል ቁጥር 15 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ። 
  6. እያንዳንዱ ተጫራች ለሚወዳደርበት የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ጫማ፣ ቋሚ ንብረት ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ ሼልፍ፣ የመኪና ባትሪዎች፣ የሞተር ና የመሪ ዘይት ወዘተ በመለየት በግልጽ መጻፍ ይኖርበታል ስርዝ ድልዝ ካለው የማንቀበል መሆኑን እንዲሁም የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በማድረግ በፖስታ በማሸግ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባትና ከጨረታው ሰነዱ ጋር በናሙና መሠረት የማቅረብ ግዴታ አለበት። 
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ15ኛው የሥራ ቀን በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም የጨረታው ሰነድ ከተሞላ ወኪል ባይገኝም የሚከፈት መሆኑን። 
  8. አሸናፊ የሆነ ድርጅት ንብረቱን በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ የሚችል። 
  9. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብት አለው። 

ስልክ ቁጥር፡- 0344400274 እና 0342415758 

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo