የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ የተቋቋመለትን ዓላማ በተቀናጀ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ሥራ በመሥራት ወጥ የሆነ ግንዛቤ ለመፍጠር በዘጋቢ ፊልምና በማስታወቂያ ሥራዎች በማስታወቂያ ዝግጅትና ስርጭት በቂ ልምድና ማስረጃ የሚያቀርብ፤በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሠርቶ ማጠናቀቅና ማቅረብ የሚችል ድርጅት በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል

በኢፌዲሪ በግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ሰሜነ ሪጅን ፅ/ቤት

ኤጀንሲ የተቋቋመለትን ዓላማ በተቀናጀ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ሥራ በመሥራት ወጥ የሆነ ግንዛቤ ለመፍጠር በዘጋቢ ፊልምና በማስታወቂያ ሥራዎች የራሱ ሚዲያ ያለውና በራሱ ሚዲያ ማሰራጨት የሚችል፤ ሚዲያው አገራዊ ተደራሽነት ያለው ፣የዘጋቢ ፊልም ፕሮዳክሽን ሥራና ስርጭት እንዲሁም የማስታወቂያ ፕሮዳክሽን ሥራና ስርጭት /ሁለቱም ሥራዎች በአንድ ሚዲያ/ ማስተላለፍ የሚችል፤ የተሟላና ጥራት ያለው የቀረጻ መሣሪያ ያለው፡፡ ለዶክመንተሪ ቀረጻ በአራቱም ሪጅኖች በአዲስ አበባ፤በኮምቦልቻ፤ጅማ እና ባህርዳር ከተሞች ለመንቀሳቀስ የትራንስፖርት መኪና ያለው/ የሚችል፤የተሟላና ዘመናዊ ስቱዲዮ ያለው፤ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤በዘጋቢ ፊልምና በማስታወቂያ ዝግጅትና ስርጭት በቂ ልምድና ማስረጃ የሚያቀርብ፤በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሠርቶ ማጠናቀቅና ማቅረብ የሚችል ድርጅት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመግዛት በተከታታይ አሠርቶ ለማስተላላፍ ስለፈለገ፡፡ ስለዚህ፡- የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ እንጋብዛለን፡፡ 

  1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድና የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣ 
  2. የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣ 
  3. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣ 
  4. በመንግሥት ግዥ ላይ ለመሳተፍ በግዥ ኤጀንሲ ድረ ገጽ ላይ የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ 
  5. ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ማስረጃ /ክሊራንስ/ ማቅረብ የሚችል፣ 
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ስ2/በሁለት/ኤንቨሎፕ ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል በማለት ኦርጅናልና ኮፒ ተብለው በግልጽ ተለይተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
  7. ተጫራቾች ብር 12,000.00 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ የተመሰከረ ቼክ /CPO/ ወይም የባንክ ዋስትና በኤጀንሲው ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡ 
  8. ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ ብር 50.00/ሃምሳ ብር ብቻ/ በመከፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይቻላል፡፡ 
  9. ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀናት ጠዋት 2፡30-6፡30 ከሰዓት ከ7፡30-11፡00 ሰዓት ድረስ ሰነዱን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የማወዳደሪያ ሰነዳቸውን ማስገባት ይችላሉ፡፡ 
  10. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡ 00 ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 4፡15 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የሚከፈትበት በዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ 
  11. በጨረታው አሸንፎ በወቅቱ ውል ለማያስሩ የጨረታ አሸናፊዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ /ሲፒኦ አይመለስም፡፡ 
  12. ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

አድራሻ፡- አራት ኪሎ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በስተጀርባ የቀድሞ ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ሕንፃ ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ 

ቁጥር፡- 011 157 0333/011 157 0366 

በፋክስ ቁጥር፡- 011 155 0369 

 

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo