የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የጤና ቢሮ የህትመት ሥራዎች እና የታብሌት ኮምፒዩተሮች ከህጋውያን ነጋዴች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

ትግራይ ክልል ጤና ቢሮ
  • የህትመት ሥራዎች እና
  • የታብሌት ኮምፒዩተሮች ከህጋውያን ነጋዴች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መስፈርቱን የምታሟሉ ህጋውያን ተወዳዳሪዎች እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡

  1. ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) እንዲሁም የታደሰ የአቅራቢች ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፤ 
  2. የቫት ምዝገባ የምስክር ወረት እና የሚያዝያ 2011 - ዓ.ም. ቫት ዲክሌር ያደረጉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤ 
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ሎት-1 የህትመት ሥራዎች/ ሲፒኦ/ CPO ብር 20,000 እና ለሎት-2 የታብሌት ኮምፒዩተሮች /ኢፒኦ/ (CPO) ብር 5,000 ማስያዝ የሚችሉ፤ 
  4. ተወዳዳሪዎች ለሎት1 [የህትመት ሥራዎች የጨረታን ፋይናንሻል ዶክሜንት አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ እንዲሁም ለሎት -2 /የታብሌት ኮምፒዩተሮች ፋይናንስ እና ቴክኒካል ዶክሜንት አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በስራ ሰዓት የግዥ ንኡስ ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር-42 ማስገባት አለባቸው፧ 
  5. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሆኖ የመክፈቻ ቀን እና ሰዓት እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መምሪያዎች በሙሉ በሚሸጠው ጨረታ ሰነድ መመልከት ይቻላል፤ 
  6. ተወዳዳሪዎች በተሰጠው ዝርዝር ስፔሲፊኬሽን መሰረት የመወዳደሪያ ዋጋቸውን መሙላት ይጠበቅባቸዋል፤
  7. ተወዳዳሪዎች የሚያስቡት ዋጋ ቫት እና የትራንስፖርት እንዲሁም ሌሎች ወጪዎች ያካተተ መሆን አለበት ካልሆነ እንዳካተተ ይቆጠራል፤ 
  8. ተወዳዳሪዎች አሸናፊ ሆነው ከተገኙ ውል ከገቡበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለሎት-1 /የህትመት ሥራዎች 60 ተከታታይ ቀናት ለሎት-2 /የታብሌት ኮምፒዩተሮች ደግሞ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. የጨረታ ሰነድ ዋጋ የማይመለስ ብር 100.00 [አንድ መቶ ብር/ ከፍለው ከክልል ትግራይ ጤና ቢሮ የግዥ ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 42 በሥራ ሰአት መግዛት ይችላሉ፤ 
  10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው እንዲሁም 20% መጨመር አልያም መቀነስ ይችላል፤ 
  11. ማንኛውም ግልፅ ያልሆነ ጥያቄ ካላችሁ ጨረታ ሰነድ የሚከፈትበት ቀን ከመድረሱ ከ5 ቀናት በፊት በጽሑፍ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣ 
  12. ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት (BID VALIDITY DATE) 60 ቀናት ይሆናል፤ 
  13. በእያንዳንዱ ንብረት አሸናፊ ይለያል በድምር ወይም በጠቅላላ አሸናፊ አይደረግም፤ 

ለበለጠ መረጃ የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ 

ስ.ቁ 03-44-40-47-15፤ ደውለው መጠየኝ ይችላሉ 

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo