ደደቢት ብድርና ቁጠባ አ/ማ ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ ጀነሬተሮች ብግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

ደደቢት ብድርና ቁጠባ ተቋም

የጨረታ ማስታወቂያ 

1. ደደቢት ብድርና ቁጠባ አ/ማ ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ ጀነሬተሮች ብግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል:: 

ስለሆነም በዚህ ጨረታ መወዳደር የምትፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች የምታሟሉ መጫረት የምትችሉ መሆናቹ እንገልፃለን:: 

2. የ2011 ዓ/ም ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ ምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ ሰርቲፊኬ (TIN) የተመዘገባችሁ መሆኑን የሚገልፅ እና የባለፈው ወር የቫት (VAT) ዲክላሬሽን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባችዋል:: 

3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ የሚሆን CPO ወይ Unconditional Bank Grantee ብር 300,000.00 /ሶስት መቶ ሺ/ ብር ማስያዝ ይኖርባችዋል:: 

4. ሁሉም ተጫራቾች ጨረታ ሰነድ 12/09/2011 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 30/09/2011 ዓ/ም በአዲስ አበባ ተክለሃይማኖት ቅርንጫፍና በመቐለ በሚገኘው ዋና መስሪያቤታችን ደደቢት ብድርና ቁጠባ አ/ማ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 409 አስፈላጊውን ማስረጃ በመያዝ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዝርዝር የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ

5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ውስጥ ያሉ ቅፆችን በትክክል በመሙላት በየአንዳንድ ገፅ በመፈረም እና ማህተም በማድረግ ምንም ገፅ ሳያጓድሉ ማቅረብ አለባችሁ:: የጎደለ ገፅ ወይም የተዛባ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል:: 

6. ተጫራቾች የተጫረቱበትን ጀነሬተሮች ቴክኒካልና ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ እንዲሁም የጨረታ ማስከበርያ ሰነድ በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ ሁሉንም በትልቅ ፖስታ በማሸግ መቐለ ዋና ቢሮ በ4ኛ ፎቅ በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል:: 

7. ጨረታው 30/09/2011 ዓ.ም ከጥዋቱ 3፡00 ተዘግቶ በድርጅቱ የቀረበውን ሰነድ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እንዲሁም የተሟላ ዶኩሜንቱ ከሆነ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በይኖሩም ከጥዋቱ 3፡30 ይከፈታል:: 

8. የጨረታው አሸናፊ ውጤት እንደተገለፀ በአምስት/5/ ቀን ውስጥ ውል ማሰር ይኖርበታል:: 

9. የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት እንደተገለፀ የመልካም ስራ አፈፃፀም ከጠቅላላ ዋጋ 10% CPO ወይ Unconditional Bank Grantee ማስያዝ ይኖርበታል:: 

10. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት በ100 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ ሙሉ በሙሉ አምጥቶ ገጥሞ ማስረከብ የሚችል:: 

11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: 

12. ለበለጠ መረጃ ዋና ቢሮ ሶስተኛ ፎቅ ቁጥር 11 ወይም በስልክ ቁጥር 0342-40-00-14 መቐለ ዋና ቢሮ በመደወል ማረጋገጥ የምትችሉ መሆናችሁን እንገልፃለን:: 

ደደቢት ብድርና ቁጠባ አ/ማህበር 

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo