የትግራይ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ የአይቲ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች IT Electronics Equipments በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

የትግራይ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ
  1.  የአይቲ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች IT Electronics Equipments በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

በመሆኑም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ እየጋበዝን የተዘጋጀው የጨረታ ዶኩመንት የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ በመክፈልግንቦት 7ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ከቢሯችን የእቃ ግዢ አስተዳደር ቡድን በሥራ ሰዓት እየመጣችሁ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ቀጥለው የተዘረዘሩትን ማሟላት ይጠበቅባችኋል:: 

  • ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ ቫት ሰርተፍኬትና ያለፈው ወር ቫት ሪፖርት የተደረገበት ማስረጃ የንግድ ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት:: 
  • ተጫራቾች የጨረታ መመሪያውን በጥንቃቄ አይተው መወዳደር አለባቸው 
  • የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በእያንዳንዱ ጨረታ ዶኩሜንት ላይ የተገለፀው መጠን በቢሯችን ስም በሲፒኦ አሰርተው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። 
  • ቢሯችን በጨረታ ከቀረበው የዕቃዎች ብዛት እስከ 15% በመቶ ለመቀነስ ወይም ለመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው። 
  • ጨረታው ሰኔ 06 ቀን 2011 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓትላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሯችን የዕቃ ግዢ አስተዳደር ቡድኑ ይከፈታል። 
  • ቢሯችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። 
  • ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች፡0344403663/ 0344404346 ወይም በፋክስ  ቁጥር 0344409971 መጠየቅ ይቻላል። 

የትግራይ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ 

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo