መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጂነሪንግ ኃላ/የተ/የግል/ኩባንያ (MIE) ንፅሕናው የጠበቀ መኝታ ቤት፣ ቢሮ ማእድ ቤት ኪችን፣ የመመገቢያ ኣዳራሽ ያለው እና እስከ 25/ ሃያ ኣምስት/ የመሽታ ክፍል ያለው ለስፖርተኞች የሚሆን መኖሪያ ቤት በጨረታ ለመወዳደር ሊከራይ ስለሚፈልግ የምትፈልጉና የሚከተሉትን መስፈርቶችን የምትሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ በኣክብሮት ይጋብዛል።

መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ ኋ/የተ/የግ/ማህበር

የጨረታው መስፈርት

1 ተጫራቾች የሚጠበቅባቸው የመንግስት ግብር የሚከፍሉ መሆን ኣለባቸው፤

2 ተጫራቾች የማይመለስ ኣንድ የታደሰ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ በማያያዝ የጨረታው ዝርዝር ሰነድ በስራ ሰኣት ከመቐለ ሳፕላይ ዋና ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።

3 ተጫራቾች የጨረታው ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ከ 08/04/2019 እ.አ.አ ጀምሮ እስከ 30/04/2019 እ.ኤ.አ ከሰኣት በኃላ 8:00 ሰዓት ጀምሮ መቐለ ዋና መስሪያ ቤት ለዚህ ተብሎ በታዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4 ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) 10000.00 /ኣስር ሺ ብር/ በስም በታሸገ ፖስታ ከጨረታ ጋር ማስገባት አለባቸው :: በፖስታ ያልታሸገ ሲፒኦ እንዲሁም ጥሬ ገንዘብ ተቀባይነት የለዉም።

5 ጨረታዉ 30/04/2019 እ.አ.ኣ ከሰኣት በ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በ 30/04/2019 እ.ኤ.አ ከሰኣት በኃላ 8:30 ሰዓት ተጫራቶች ወይም ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በመቐለ መስፍን ዋና መ/ቤት በሚገኝ የስብስባ አዳራሽ የሚከፈት ሲሆን ሰነዳቸዉ የተሞላ ከሆነ ባይገኙም ጨረታ ሰነዱ ይከፈታል።

6 ኣሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራቸው ቀን ጀምሮ 05 ቀናት ውስጥ የውል በማሰር ቤቱን ማከራየት ኣለባቸው። ይህ ካልሆነ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ብር ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ድርጅቱ ሌላ ኣማራጭ ይወስዳል።

7 ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ተመስርተው ዋጋ ማስገባት ኣይፈቀድም፡፡

8 ተጫራቾች ይህን ጨረታ ካሸነፉ ለሌላ ሶስተኛ ወገን ኣሳለፎ መስጠት ኣይችሉም፡፡

9 ተጫራቾች የሚያቀርቡት የክራይ ቤቱ መቐለ ከተማ ሚገኝ ሆኖ የክፍሉ ንፅህናው መጠበቅ ኣለበት፡፡

10 ድርጅቱ ለኣሸናፊ ተጫራቾች የኣንድ ኣመት ክራይ ዋጋ ውል ካሰሩት ቀንና ድርጅት ቤቱን ከተረከበበት ቀን ጀምሮ ባሉት ኣምስት/5/ የስራ ቀናት ውስጥ ይከፈላቸዋል፡፡

11 ኩባንያዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በክፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነዉ:

ለበለጠ መረጃ ስ.ቁጥር መቐለ +251 0344-406803/6225 ፋክስ 00251 344406225

ኣዲስ ኣበባ ስ.ቁጥር +251-114709792/+251-116298560 መደወል ይቻላል፡፡

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo