የትግራይ ልማት ማህበር በአክሱም ከተማ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ማእከልና የወጣቶች መዝናኛ ማዕከል ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

የትግራይ ልምዓት ማሕበር

1.ደረጃቸው GC/BC-3 ከዚያ በላይ የሆኑ የ2011 ዓ.ም የኮንስትራክሽን ፍቃዳቸውንና የንግድ ስራ ፈቃዳቸው ያሳደሱ፣ በኮንስትራክሽን አቅራቢነትና ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የቫት ሰርተፍኬት፣ የቲን ሰርተፍኬትና የመጨረሻ ወር የቫት ዲክላሬሽን የሚያቀርቡ፣ ቴክኒካል ዶክመንት ጋር ተያይዞ ካልቀረበ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡

2.የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች 150,000.00 (አንድ መቶ አምሳ ሺህ ብር) በሲፒኦ ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3.ተጫራቾች ለሚሰሩት የህንጻ ፕሮጀክት ሳይት ከተረከቡበት ቀን ጀምሮ በ730/ሰባት መቶ ሰላሳ/ ተከታታይ ቀናት አጠናቆ ማስረከብ የሚችሉ፣

4.የጨረታው ዶክመንት ከ16/07/2011 ዓ.ም  ጀምሮ እስከ 11/08/2011 ዓ.ም አስፈላጊውን ዶክመንት (በተራ ቁጥር አንድ ላይ የተዘረዘሩት) በመያዝ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከትግራይ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 435 መውሰድ ይችላሉ፡፡

5.የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ፣ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክምንቶች ኦርጅናሉና ሁለት ፎቶ ኮፒዎች፣ ሲፒኦ ለየብቻቸው በፖስታ ታሽገው በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በላዩ ላይ ለሚጫረቱት ፕሮጀክት ስም በሚታይ ቀለም ጽፈው በሁሉም ዶክመንት(አጠቃላይ ላይ ተፈርሞበትና ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት እስከ 11/08/2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት በትግራይ ልማት ማህበር ዋናው ጽ/ቤት ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6.ከት/ል/ማ ህንጻ ፕሮጀክት ወስዶ ይህ የጨረታ ሰነድ አየር ላይ እስከዋለበት ቀን ድረስ ፊዚካል አፈጻጸሙ ከ70% በታች የሆነ ፕሮጀክት ያለው ተጫራች ጨረታ ዶክመንት መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም፣ 

7.ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባሉበት 11/08/2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በተጠቀሰው ቦታ ይከፈታል፡፡

8.አሰሪው ጽ/ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

9.ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር -034 440 68 40 መጠየቅ ይቻላል፡፡

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo