የመቀሌ የአካባቢና የደን ምርምር ማዕከል የፅህፈት መሳርያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የኮምፒተርናየኮምፒተር ተዛማጅ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ እንዲሁም የፈርንቸር ዕቃዎች አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል

የመቀሌ የአካባቢና የደን ምርምር ማዕከል
  • የፅህፈት መሳርያዎች፣
  • ኤሌክትሮኒክስ፣
  • የኮምፒተርና፣የኮምፒተር ተዛማጅ ዕቃዎች፣
  • የፅዳት ዕቃዎች፣ እንዲሁም
  • የፈርንቸር ዕቃዎች አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል።
  1. የ2011 ዓ.ም የዘመኑን ግብር የከፈለና የንግድ ፍቃድ የታደሰ ማቅረብ የሚችል።
  2. የቫት ምስክር ወረቀትና የጥር ወር ዲክለሬሽን ማቅረብ የሚችል።
  3. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርቲፊኬትና ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችል።
  4. የታደሰ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
  5. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ ከ8/7/2011 እስከ 24/7/2011 ዓ.ም በአካል በማቅረብ ለፅህፈት መሳርያ 30 ብር፣ ለኤሌከትሮኒክስ፣ ለኮምፒተርና ለኮምፒተር ተዛማጅ 30 ብር፣ ለፅዳት ዕቃዎች 20 ብር፣ ለፈርንቸር 20 ብር፣ በመክፈል ከግዥ ቡዱን ቢሮ ቁጥር 01 በስራ ሰዓት መውሰድ የምትችሉመሆኑን እንገልፃለን።
  6. ተጫራቾች ኦርጅናልና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በማዕከላችን በሚገኘው የግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በተዘጋጀው ሣጥን እስከ ጥዋቱ 4:00 ማሰገባት የሟችሉ መሆኑን እንልፃለን።
  8. ጨረታው በ24/7/2011 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ24/7/2011 ዓ.ም 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫረቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ባይገኙ ማዕከሉ ጨረታውን የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ተጫራቾች ያሸነፉት ዕቃዎች በ10 ቀን ውስጥ ስራሳቸው ትራንስፖርት ዓዲሹምድሑን መጨረሻ ታክሲ አካባቢ በሚገኘው የማዕከላችን መስሪያ ቤት ገቢ ማድረግ አለባችሁ።
  10. ማዕከላችን ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ60 ቀናት ይሆናል።
  12. ማዕከላችን ጨረታው 20% የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው።
  13. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ከነ ቫቱ ማዕከሉ ባዘጋጀው ሰንጠረዥ ማስቀመጥ አለባቸው።
  14. ተጫራቾች የሰነዱ ዋጋ በሚሞሉበት ጊዜ የድርጅቱ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ መፃፍ አለባቸው። እንዲሁም የታወቁ ጉዳቶች የገንዘብ መጠን 1/1000 የሚቀጣ ይሆናል።
  15. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለፅህፈት መሳሪያ 2,200 ብር (ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ብር) ለኤሌክትሮኒክስ፣ ኮምፒተርና ኮምፒተር ተዛማጅ 1,400 ብር /ኣንድ ሺህ አራት መቶ ብር/ ለፈርንቸር 600 ብር /ሰድስት መቶ ብር/ና ለፅዳት ዕቃዎች 1,000 ብር /አንድ ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ ሲፒኦ /Unconditional CPO/ ማቅረብ አለባቸው።

ለበለጠ መረጃ ለመቀሌ የአካባቢና የደን ምርምር ማዕከል ዓዲሹምድሑን መጨረሻ ታክሲ በሚገኘው የማዕከላችን ቢሮ በአካል በመቅረብ ወይምበስልክ ቁጥር 034 240 03 75 መጠየቅ ይቻላል

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo