መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጂነሪንግ ኃላ/የተ/የግል/ኩባንያ (MIE) Steel pipe Ø 114x 4.5x 6000mm እና sheet Metal 3000x1500x3mm በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ብቃት ያላችሁ እና ከዚህ በታች የተዘረዝሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎችን እንድትሳተፉ ኩባንያውን በኣክብሮት ይጋብዛል።

መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ ኋ/የተ/የግ/ማህበር

የጨረታው መስፈርት

1 ተጫራቾች በዘርፉ የ2011ዓ/ም የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው : የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የወሩ ቫት ማሳወቂያ ኦርጂናል እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በማያያዝ ከ06/03/2019 እ.ኤ.ኣ ጀምሮ እስከ 26/03/2019 እ.ኤ.አ የጨረታው ሰነድ በስራ ሰኣት ከመቐለ ወይም ኣ/ኣበባ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት መውሰድ ይችላሉ።

2 ተጫራቾች የጨረታው ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ከ 06/03/2019 እ.አ.አ ጀምሮ እስከ 26/03/2019 እ.ኤ.አ ከሰኣት በኃላ 8:00 ሰዓት ጀምሮ መቐለ ዋና መስሪያ ቤት ወይም ኣዲስ ኣበባ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ለዚህ ተብሎ በታዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።ከሰኣቱ በኃላ ከቀኑ ልክ 8፡00 ሰኣት ካለፈ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

3 ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ለ sheet Metal 3000x1500x3mm  40000.00 (ኣርባ ሺ ብር)፣ ለ Steel pipe Ø 114x 4.5x 6000mm 10000.00 /ኣስር ሺ ብር/ በስም በታሸገ ፖስታ ከጨረታ ጋር ማስገባት አለባቸው :: በፖስታ ያልታሸገ ሲፒኦ እንዲሁም ጥሬ ገንዘብ ተቀባይነት የለዉም።

4 ጨረታዉ 26/03/2019 እ.አ.ኣ ከሰኣት በ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በ 28/03/2019 እ.ኤ.አ ከሰኣት በኃላ 8:30 ሰዓት ተጫራቶች ወይም ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በመቐለ መስፍን ዋና መ/ቤት በሚገኝ የስብስባ አዳራሽ የሚከፈት ሲሆን ሰነዳቸዉ የተሞላ ከሆነ ባይገኙም ጨረታ ሰነዱ ይከፈታል።

5 ተጫራቾቸ የሚያስገቡት ዋጋ ቫት (VAT) ጨምሮ መሆኑና ወይም አለመሆኑን መጠቀስ አለበት ::ይህ ካልሆነ ያስገቡት ዋጋ ቫት (VAT) እንደሚያካትት ተቆጥሮ ይወሰዳል።

6 ኣሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራቸው ቀን ጀምሮ 05 ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ እቃ የጠቅላላ ቫትን ጨምሮ 10% የውል ማስከበሪያ የባንክ ዋስትና ( Unconditional bank guarantee) ወይም ሲፒኦ በማሰራት ከኩባንያው ጋር ውል መፈራረም ኣለባቸው። ይህ ካልሆነ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ብር ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ድርጅቱ ሌላ ኣማራጭ ይወስዳል።

7 ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ መጓጓዣ፣ የመጫኛና የመውረጃ ያካተተ መሆን ኣለበት። ኣሸናፊው ተጫራቾች ጨረታውን ኣሸንፈው ውል ካሰሩ ቀን ጀምሮ አያንዳንዱ እቃ በ30 ቀናት ውስጥ ማስረከብ ኣለባቸው። ክፍያ በተመለከተ ያቀረቡት እቃ በድርጅታችን ጥራት ቁጥጥር ታይቶ ተተቀባይነት ካገኘ በኃላ በኣስር ቀናት ውስጥ የሚፈፀም ይሆናል፡፡

8 ዕቃው የሚራገፍበት ቦታ መቐለ

9 ኩባንያዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በክፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነዉ:

ለበለጠ መረጃ ስ.ቁጥር መቐለ +251 0344-406803/6225 ፋክስ 00251 344406225

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo