በአገር መከላከያ ሚ/ር በሰሜን ዕዝ ስር 4ኛ ሜ/ክ/ጦር መኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የተለያዩ አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎችና የጀኔሬተር መለዋወጫ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

በሀገር መከላከያ ሚኒስትር የሰ/ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ

ሎት 1. የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣

ሎት 2. የፅዳት ዕቃዎች፣

ሎት 3. የተለያዩ አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎችና

ሎት 4. የጀኔሬተር መለዋወጫ ዕቃዎች

1 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በዚህ መሠረት በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ በ2011 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት የቫት (VAT) ሰርተፍኬት ያላቸውን ይጋብዛል። ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መመሪያ እና ዝርዝር ሰነድ የያዘ ለእያንዳንዱ ሎት 50.00/ሃምሣ ብር በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ኩሓ ማይ ባንዲራ በሰሜን ዕዝ ስር የ4ኛ ሜ/ክ/ጦር ከሚገኘው ግዥ ዴስክ ቢሮ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን  በመግዛት በቢሮ ወደ ተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ጨረታው ከጥር 29 ቀን 2011 እስከ የካቲት 14 ቀን 2011 ዓ.ም በዚያዉ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚህ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም ይከፈታል።

2 መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0342400166 / 0344420309
በአገር መከላከያ ሚ/ር በሰሜን ዕዝ የ4ኛ ሜ/ክ/ጦር መምሪያ

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo