ሎት 1 ሞተር ሳይክል፣
*ሎት 2 ዲስክቶፕ ኮምዉፒተር
1. በዘርፉ የ2011 ዓ.ም ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ፤ ቲን ነምበር ፣ ቫት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፡፡
2. የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል/በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር አቅራቢዎች ዝርዝር ዉስጥ መመዝገባቸዉ የምስክር ወረቀት /በ Website ዝርዝራቸዉ ያለና ማቅረብ የሚችል፡፡ ሕዳር ወር ዲክለር ያረጉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
3. ተጫራቾች ከ19/4/2011 ዓ.ም እስከ 6/5/2011 ዓ.ም ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ትግራይ ክልል ከተማ ልማት ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 59 የማይመለስ ብር 50.00/ሃምሳ ብር/ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
4. ጨረታዉ ዕለት 6/5/2011 ከቀኑ 5፡00 ታሽጎ በተመሳሳይ ቀን 5፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሞተር ሳይክል ብር 50,000 /ሀምሳ ሺ ብር/ ለዲስክቶፕ ኮምፒዉተር 10,000/አስር ሺ/ በሲፒኦ ወይም በምክንያት ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ማስያዝ የሚችሉ፡፡
6. ተጫራቾች እቃዉ የሚሸጡበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦርጅናል 1 ኮፒ 1 በማድረግ ለየብቻዉ በማሸግ ማስታወቂያዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በትግራይ ክልል ከተማ ልማት ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 59 ሰነድ ማስገባት ይቻላል፡፡
7. ተጫራቾች ሰነድ ላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እያንዳንዱን የተቀመጠ ዋጋ ከነቫቱ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
8. በጨረታዉ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በእያንዳንዱ የተቀመጠ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ካለዉ ከጨረታዉ ዉጪ ይሆናል፡፡ በእያንዳንዱ ገፅ ማህተምና ፊርማ መኖር አለበት፡፡ ሰነድ ጨረታ በሙሉም ሆነ በከፊል ማስቀረት ከጨረታ ዉጪ ያደርጋል፡፡
9. ቢሮዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
ለተጨማሪ መተጃ በስልክ ቁጥር +251-03-42-40-01-29 ወይም 0344408973
ፋክስ ቁጥር 0344 41 58 59