ፋብሪካችን ሞሓ የለስላሳ መጠጦች ኢንዳስትሪ አክስዩን ማህበር መቐለ ፔፕሲ ኮላ ፋብሪካ የተለያዩ ዓይነት የአደጋ መለካከያ ( ሴፍቲ ማተሪያልስ) እና የፅዳት ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ሞሃ የስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ S,C

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መምርያ ኣክብራችሁ መወዳደር የምትችሉ ተጫራቾች ሁሉ መጫረት የምትችሉ መሆኑ በኣክብሮት እንገልፃለን።

የጨረታ መምርያ

1 ተጫራቾች በዘርፉ የ2010ዓ/ም የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ : የኣቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት: የቫት ተመዝጋቢ መሆኑ የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት እና ቲን ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2 ተጫራቾች ለጨረታዉ ማስከበሪያ የጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 2% የገንዘብ ክፍያ ማዘዣ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል ።

3 ተጫራቾች የሚቀርቡትን ዋጋ ቫት ያካተተ ሙሆኑን እና አለመሆኑን በግልፅ መቀመጥ ይኖርባቸዋል። ይህ ካልሆነ ግን ዋጋዉ ቫትን ያካተተ መሆኑ ታሳቢ ይደረጋል።

4 የጨረታዉ ዝርዝር ሰነድ ከድርጅቱ  ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 15 ድረስ በመምጣት እና የማይመለስ ብር 50.00 በመክፈል መውሰድ ይቻላል።

5 በጨረታ ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት ኣይኖረዉም።

6 ተጫረቾች ዋጋቸዉ በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህን ጨረታ ከወጣበት ግዜ ጀምሮከ 22/03/2011ዓ/ም እስክ ከ 10/04/2011 ዓ/ም በስራ ቀንና ሰዓት ኣክሱም ሆቴል ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ዋና ቢሮኣችን ድረስ በመምጣት ለዚሁ ተብሎ በተዘገጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ እና የሰነዱ ማሽግያ ፖስታ ተጫራቾች ህጋዊ ማህተምና እና ፊርማ መኖር ይኖርበታል።

7 የጨረታ ሳጥኑ ታሕሳስ10/04/2011 ዓ/ም ከቀኑ 8:15 የሚታሸግ ሲሆን ከዚሁ ሰዓት ባኃላ የጨረታ ሰነድ የሚመጣ ተቀባይነት ኣይኖረዉም።

8 ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት/ ባልተገኙበትም 10/04/2011 ዓ/ም ከቀኑ ልክ 8:30 በፋብሪካዉ የግዥና ክምችት መምሪያ ቢሮ ወስጥ ይከፈታል።

9 ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ላይ ያሸነፈቸዉን የእቃ አይነቶች ማሸነፋቸዉ እንደተነገራቸዉ በ 3 ቀናት ወስጥ ላሸነፉዋቸው እቃዎች የጠቅላላ 10% ሲፒኦ በማሰራት ለውል ማስከበሪያ በማቅረብ ውል የማሰር ግዴታ ኣለባቸው።

10 ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ላይ ያሸነፈቸዉን የእቃ አይነቶች ማሸነፋቸዉ እንደተነገራቸዉ በ7 ቀናት ወስጥ እቃዎችን የማስረከብ ግዴታ ይኖርባቸዋል።ይህ ሳይሆን ሲቀር ግን ያስያዘዉ የዉል የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ካለ ምንም ቅድመ ሆኔታ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።

11 ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ ከተከፈተ ባኃላ ጨረታዉን መሰረዝ ኣይችልም።

12 ስርዝ ድልዝ የሆነ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም።

13 ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በማንኛዉም ግዜ ጨረታዉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo