በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የማዕከላዊ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የሞያተኛ የእጅ መገልገያ ዕቃዎች፣ የሙዚቃ መሣሪያ መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የኔትወርክ ዕቃዎች፣ የቧንቧ ዕቃዎች፣ አቡጀዴና ሻሽ፣ የመኪና ባትሪና የባትሪ ኮኔክተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

በሀገር መከላኪያ ሚኒስቴር የ4ኛ ደረጃ ሜንቴናንስ ሽሬ ኮሪደር

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የማዕከላዊ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  1. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
  2. የሞያተኛ የእጅ መገልገያ ዕቃዎች
  3. የሙዚቃ መሣሪያ መለዋወጫ ዕቃዎች
  4. የኔትወርክ ዕቃዎች
  5. የቧንቧ ዕቃዎች
  6. አቡጀዴና ሻሽ
  7. የመኪና ባትሪና የባትሪ ኮኔክተር

ስለዚ  ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች በጨረታው ሊወዳደር ይችላል።

  1. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው የጨረታ ዓይነቶች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ( ከፋይነት) ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የንግድ መዝገባ የምስክር ወረቀት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ለእያንዳንዱ ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለጸው መመሪያ መሰረት በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የዕቃውን ዓይነት ኤንቨሎፕ ላይ በግልፅ መፃፍ ይኖርባቸዋል።
  6. የጨረታ ሰነዱን ከተጫራቾች ዝርዝር መመሪያ ጋር የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል ይህ  ማስታወቂያ በጋዜጣ ታውጆ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት ቀናት ውስጥ ሽሬ እንደሥላሴ በሚገኘው የማዕከላዊ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ግዥ ቡድን ቢሮ መግዛት ይቻላል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ሽሬ ከተማ በሚገኘው ማ /ዕዝ ጠ/ መምሪያ መዝናኛ ክበብ ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. ጨረታው ህዳር 17 ቀን 2011 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማ/ዕዝ መዝናኛ ክበብ ውስጥ ይከፈታል።
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈፅሙ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ያሸነፉበትን ዕቃ በራሳቸው ወጭ በማጓጓዝ  እና በማራገፍ ሽሬ እንደሥላሴ ከተማ በሚገኘው የማዕከላዊ ዕዝ ጠቅላይ መመሪያ ግምጃ ቤት ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ፣ እንዲሁም 20%  ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 034-844-07 60 ይደውሉ።

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo