የትግራይ ክልል የወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ ለስፖርት ውድድር አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የስፖርት ዓይነት ትጥቆችና የስፖርት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

የትግራይ ወጣቶችና እስፖርት ቢሮ

የትግራይ ክልል የወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ በ2011 ዓ.ም ለስፖርት ውድድር አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የስፖርት ዓይነት ትጥቆችና የስፖርት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  1. ተጫራቾቹ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና ፈቃዳቸውን ያሳደሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና በየወሩ ለግብር ሰብሳቢ አካል የከፈሉ መሆናቸውን/ዲክለሬሽን/ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም የታደሰ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሚያቀርበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተተ መሆኑን በግልጽ ካላስቀመጠ ተጨማሪ እሴት ታክስ አካቶ እንደተሞላ ይቆጠራል፡፡
  4. ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ትግራይ ክልል ወጣቶች ስፖርት ጉዳይ /ቢሮ ቁጥር 23 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላል።
  5. የጨረታ ሰነዱ በአማርኛ ቋንቋ የሚሞላ ሆኖ በግልጽ በሚነበብ ሁኔታ የተዘጋጀና ስርዝ ድልዝ የሌለበት መሆን ይኖርበታል።
  6. የጨረታ ሰነድ በጨረታ ከወጣበት ከ12/02/2011 እስከ 12/03/2011 ዓ.ም የትግራይ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ /ቢሮ ቁ. 23 በስራ ሰዓት በመገኘት መውሰድ የሚቻል መሆኑን በተመሳሳይ ጊዜ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የድርጅቱ ስም ፊርማ ማህተም በማስፈር ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል።
  7. የጨረታ ሳጥን በ12/03/2011 ዓ.ም 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ12/03/2011 ዓ.ም 9፡30 ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑና ተወካዮች ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት የሚያዳግት ነገር አይኖርም።
  8. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ጊዜ በኋላ ባሉት ሦስት ቀናት ውስጥ ውል ማሠር ይኖርበታል።
  9. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች ውል ካሰሩ በኋላ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ዕቃው የትግራይ ክልል የወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ በመቀሌ ከተማ ባለው ጽ/ቤቱ በራሱ ትራንስፖርት አቅርቦ የማስረከብ ግዴታ አለበት።
  10. ቢሮው በሚገዙት ዕቃዎች ላይ እንደ አስፈላጊነቱ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው።
  11. የጨረታ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ባሉት ቀጣይ 60 ቀናት ይሆናል።
  12. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
  13. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0344408877 በመደወል ወይም መቐለ ከተማ በሚገኘው የትግራይ ክልል የወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ ቁጥር 23 በአካል በመገኘት መጠየቅ ይቻላል።

የትግራይ ክልል የወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ ፊት ለፊት ደደቢት ማይክሮ ፋይናንስ ኮምፕሌክስ ሕንፃ

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo