የሰቲት ሑመራ ዕቅድና ፋይናንስ ፅህፈት ቤት ለ2011 በጀት ዓመት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል የፅህፈት መሳሪያዎች፣የህትመት እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ አላቂ ንብረት፣የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች እና ተሽከርካሪ መግዛት ይፈልጋል።

የሰቲት ሑመራ ከተማ እቅድና ፋይናንስ ጽህፈት ቤት

የከተማ ሰቲት ሑመራ ዕቅድና ፋይናንስ ፅህፈት ቤት ለ2011 በጀት ዓመት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል ንብረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ አቅራቢዎች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ከመንግስት ግዠና ንብረት አስተዳደር በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ የሆነ።
  3. ተጫራቾች የግብር ከፋይ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. የነሐሴ 2010 ዓ.ም ወይም መስከረም ወር 2011 ዓ.ም ቫት ድክሌር ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡
  5. ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ግዥ ንብረት የ6ት ወር /ስድስት ወር/ ዋስትና መስጠት የሚችል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ እንደ ተጫራቹ ምርጫ በጥሬ ገንዘብ ወይም CPO ማስያዝ የሚችል።

    6.1 ከሎት አንድ ያሉ ዝርዝር ዓይነት ንብረቶች የፅህፈት መሳሪያዎች ለሎት አንድ 25000 ብር /ሃያ አምስት ሺ ብር/

    6.2 ሎት ሁለት የህትመት እቃዎች ለሎት ሁለት 5000ብር /አምስት ሺ ብር/

    6.3 ሎት ሶስት የፅዳት እቃዎች/ ሎት ሶስት 3500 ብር /ሶስት ሺ አምስት መቶ ብር/

    6.4 ሎት አራት አላቂ ንብረት ለሎት አራት 20,000 ብር /ሃያ ሺ ብር/

    6.5 ሎት አምስት የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ለሎት አምስት 35000 ብር /ሰላሳ አምስት ሺ ብር/

    6.6 ሎት ስድስት የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች እና ተሽከርካሪ መግዣ 15000 ብር /አስራ አምስት ሺ ብር/ ለብቻው በፖስታ ታሽጎ ፖስታው ላይ ማህተም፣ ፊርማ ስምና አድራሻ አድርጎ ማስያዝ የሚችል፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፈው ዝርዝር ንብረት በራሳቸው ትራንስፖርት በትግራይ ክልል በምዕራባዊ ዞን ሰቲት ሁመራ ከተማ ዕቅድና ፋይናንስ ጽህፈት ቤት ማስረከብ የሚችሉ።
  8. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በግልፅ ኦርጅናል የጨረታ ሰነድ ላይ ሞልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት /15/ ቀናት ተከታታይ ቀናት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. ጽህፈት ቤቱ 20% በውል ላይ መጨመርም መቀነስም ይችላል፡፡ ጨረታ ሰነዱ በሁመራ ከተማ ዕቅድና ፋይናንስ ጽህፈት ቤት ግዢ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቁጥር 25 በመምጣት 100.00 ብር በመክፈል መግዛት ይችላል፡፡
  10. መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ የድርጅቱ ህጋዊ ማህተምና፣ ፊርማ ፣አድራሻ፣ ስም፣ ስልክ ቁጥር አድርጎ የማያቀርብ ተጫራች ከጨረታ ውጪ ይሆናል።
  11. ተጫራቾች የሚጫረቱበት የመጫረቻ ሰነድ አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ ለየብቻቸው ሆኖ መቅረብ ይኖርበታል። በተጨማሪም ለየብቻው የታሸገ ሆኖ በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የተጫራቾች ህጋዊ ማህተምና ፣ፊርማ ፣አድራሻ፣ ስም፣ ስልክ ቁጥር በማድረግ ሶስቱም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ በትልቁ ፖስታ ህጋዊ ማህተምና ፣ፊርማ ፣አድራሻ፣ስም፣ ስልክ ቁጥር በማድረግ ማቅረብ ይኖርበታል።
  12. ተጫራቶች የሚሞሉት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው በጎኑ ፊርማ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን ያለማድረግ ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡፡
  13. የሚገዙ የግዥ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን / ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዘዋል ይመልከቱት፡፡
  14. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተማ ሰቲት ሑመራ ዕቅድና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 25 ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።
  15. የጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት 45 ቀናት ይሆናል፡፡
  16. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ከነ ቫቱ መሆኑ እና አለመሆኑ ማመላከት አለባቸው።
  17. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች እቃውን በ 15 ተከታታይ ቀናት ማስረከብ ይኖርበታል።
  18. ጽህፈት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
  19. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0344480062/63 መደወል ትችላላችሁ።

የሰቲት ሑመራ ዕቅድና ፋይናንስ ፅህፈት ቤት

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo