የትግራይ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ጋብዮን፣ የእርሻና ችግኝ ጣቢያ መገልገያ መሣሪያዎች፣የጽህፈት መሣሪያዎች ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ ሕትመት፣የጽዳት እቃዎች ፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋ

የትግራይ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ

ሎት 1. ጋብዮን

ሎት 2. የእርሻና ችግኝ ጣቢያ መገልገያ መሣሪያዎች

ሎት 3. የጽህፈት መሣሪያዎች

ሎት 4. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች

ሎት 5. ሕትመት

ሎት 6. የጽዳት እቃዎች

ሎት 7. የኤሌክትሪክ እቃዎች

1 በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ እየጋበዝን፣ የተዘጋጀውን የጨረታ ዶኩሜንት ለያንዳንዱየማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል ጀምሮሕጋዊ የንግድ ፈቃዳችሁን በመያዝ ከቢሮአችን የዕቃ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 በሥራ ሰዓት እየመጣችሁ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፣ በጨረታው ለመሳተፍ ቀጥለው የተዘረዘሩትን ማሟላት ያስፈልጋል።

2 የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የVAT ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin) እና ያለፈው ወር ቫት (VAT) ዲክለር የተደረገበት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መቅረብ አለበት። ተጫራቾች የጨረታ መመሪያውን በጥንቃቄ አይተው መወዳደር አለባቸው።

3 የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በጨረታ ዶኩመንቱ ላይ የተጠቀሰው መጠን ገንዘብ በCPO አሰርተው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4 ቢሮአችን በጨረታ ከቀረበው የዕቃዎች ብዛት እስከ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።

5 ጨረታው በ14/2/2011 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያውኑ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮአችን የዕቃ ግዥ ክፍል ይከፈታል።

6 ቢሮአችን የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

7 ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች 03 44 40 36 63/03 44 40 43 46 ወይም በፋክስ ቁጥር 03 44 40 99 71/03 44 40 36 63 መጠየቅ ይቻላል።

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo