የኢትዩጰያ ግብና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ የተንቀሳቃሽ መጋዘን የወለልና አርማታ (Mobile Storage Unit Slab Construction) ተያያዥነት ያላቸዉ ስራዎች ማሰራት ይፈልጋል

የኢትዩጰያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ትግራይ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት

1 የግንባታ ቦታዎች የሚካሄድባቸዉ አካባቢዎች እንደሚከተለዉ ይሆናል

ክልል ትግራይ ሰሜን ምዕራብ ዞን ወረዳ ታህታይ ኣዲያቦ ቀበሌ ማይ ኮሆሊ የሳይት ስም ሙሴ : ምዕራብ ዞን ወረዳ ፀገዴ ፍረ ቃልሲ የሳይት ፍረ ቃልሲ : ምዕራብ ዞን ወረዳ ቃፍታ ሁመራ ቀበሌ አደባይ የሳይት ስም ባከር

1 ተጫራቾች በጨረታዉ ለመወዳደር በግንባታ የሥራ ፍቃድ ዘርፍ የተሰማሩ የታደሰ የንግድ ፍቃድና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

2 የግንባታ ሥራ ፈቃድ እና ብቃት የሚረጋግጥ ከደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ ማቅረብ የሚችሉ

3 በግንባታ ዘርፍ ስራ ላይ ቢያንስ ሁለት የግንባታ ስራዎች በአመርቂ ሁኔታ ሰርቶ ያሰረከበ

4 ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ

5 የኣቅራቢነት ምዝግባ ምስክር ወረቀት ወይም በግዥ ኤጀንሲ ዌብሳይት ላይ የተመዝገቡ

6 የግብር ግዴታቸዉን ስለመወጣታቸዉ የሚያሳይ ማርጋገጫ

7 ኣንድ የግንባታ መሃንዲስ እና ኣንድ የግንባታ ፎርማን ለስራዉ መመደብ የሚችሉ እንዲሁም የነዚህን ባለሙያዎች የትምህርት ማስረጃ እና ተያያዥ የስራ ልምድ ማስረጃ ከጨረታዉ ጋር አብረዉ ማቅረብ የሚችሉ

8 ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዳቸዉን ሲያቀርቡ የፋይናንስና ቴቴክኒካል ሰነዳቸዉ በተለያየ በሰም በታሸገ ፖስታዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል

9 ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15000 በባንክ በተረጋገጠ ስፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸዉ የባንክ ዋስትና የሚያስዙ ከሆነ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀን የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል የኢንሹራንስ ሰነድ ተቀባይነት የለዉም

10 ጨረታዉ ጉንበት 22 ቀን 2010 ዓም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች የቴክኒካል እና የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ብግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ቢሮ የመሰብሰቢያ ኣዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በይፋ ይከፈታል

11 በኣማርኛ ቆንቆ የተዛጋጀዉን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣባት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ከግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት መዉሰድ ይችላሉ

12 መስሪያ ቤቱ ተሸላ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ

ለበለጠ ማብራሪያ 251 0342405314 / 251 914 703 311 / 251 911646029

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo