ድርጅታችን ማይጨዉ ፓርቲክል ቦርድ ፋብሪካ በፋብሪካዉ ግቢዉ ዉስጥ ተጠራቅመዉ የሚገኙ የጥራት ችግር ያለባቸዉ የተለያዩ መጠን ያላቸዉ ሮዉ ቦርድ ያገለገሉ የመኪና ጎማዎች ቁርጭራጭ ብረታ ብረት የኮምፒዉተር ኣክሰሰሪዎች ፕሪንተሮች ቆርቆሮ ባዶ በርሚሎችና በርከት ያሉ ስማቸዉ ከታቸ የተዘረዘሩትን ንብረቶች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

ማይጨው ፓርቲክል ቦርድ ኋ/የተ/የግ/ማህበር

ስለሆነም በጨረታ ለመሰተፍ የምትፈልጉ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸሁ የንግድ ማህበረሰብ ኣባላት ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 12 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ በፋብሪካዉ ዋና መ/ቤት ከሚገኘዉ የፋይናንስ መምሪያ ቢሮ በመምጣትና በተጨማሪም መቀሌ ከሚገኘዉ ቀበሌ 16 ፎቶ ደሰታ ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ቅ/ፅ/ቤታችን የንብረቶቹ ዝርዝር የያዘ ሰነድ በመዉስድ መጫረት የምትችሉ መሆነን እየገለፅን ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ያማሉ መሆን ይኖርባቸዋል

1 ተጫራቾች ህጋዊ የሆነ ንግድ ፋቃድ ያላቸዉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸዉ:: ለበለጠ የሰነድ ማረጋገጫቸዉን ኦርጅናል ኮፒ ማቅረብ አለባቸዉ

2 ለጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች መመልከት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በፋብሪካዉ ቅጥር ግቢ በመገኙት ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 12 ተካታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ቀርበዉ ማየት ይችላሉ

3 ንብረቱን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ከፋብሪካችን ዋና መስሪያ ቤት ከፋይናንስ መምሪያ ወይም ቀበሌ 16 ፎቶ ደሰታ ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ቅ/ፅ/ቤታችን ቀርበዉ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል መዉስድ ይችላሉ

4 ተጫራቸች መግዛት የሚፈልጉትን ዕቃ ዋጋ በመግለፅ በታሸገ ፖስታ እስክ ጥር 28/2010 ዓም 8:00 ሰዓት ድረስ በፋብሪካችን በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀዉን ሳጥን ማስገባት አለባቸዉ

5 ጨረታዉ ጥር 28/2010 ዓም ልክ 9:00 ሰዓት በፋብሪካችን ዋና መ/ቤት ሰፕላይ መምሪያ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል

6 ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዝብ ወይም በስፒኦ ብር 10,000 ማስያዝ ይኖርባቸዋል

7 ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ዕቃ ሙሉ ክፍያ በመፈፀም በ 10 ቀናት ወስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል :: በተጠቀሰዉ ጊዜ ገደብ ካላነሱ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ በቅጣት ለፋበሪካዉገቢ ተደርጎ አሸናፊነታቸዉ ይሰረዛል

8 ፋብሪካዉ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ

9 ለበለጠ ማረጃ በስልክ ቁጥር ዋና ቢሮ 034 777 1259 መቀሌ ቅ/ፅ/ቤት 034 24006393

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo