በትግራይ ክልል የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ከምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም /FSRP/ በጀት ድጋፍ ለፕሮግራሙ ተጠቃሚ ወረዳዎች አገልግሎት የሚውሉ የሰብል ማጨጃና መውቂያ የእርሻ መሣሪያዎችን እና የተለያዩ የጓሮ አትክልት ዘሮች ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

የትግራይ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር 1.ET-TIGRAY-FESRP-4681 51-GO-RFB , 2.ET-TIGRAY-FSRP-468152-GORFB በትግራይ ክልል የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ከምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም/FSRP/ በጀት ድጋፍ ለፕሮግራሙ ተጠቃሚ ወረዳዎች አገልግሎት የሚውሉ የሰብል ማጨጃና መውቂያ የእርሻ መሣሪያዎችን ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በጨረታ የሚፈጸም ግዥ ዝርዝር መግለጫ፡

ተ.ቁየዕቃው አይነትመለኪያብዛትየጨረታ ማስከበሪያ በብር
017-Threshers & 10- Reaper/ Walking harvestersቁጥር17300,000 /ሶስት መቶ ሺህ ብር/
02የተለያዩ የጓሮ አትክልት ዘሮችኪ/ግ

1200200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/

1. ስለዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ለማቅረብ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።

በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለበት ማስረጃ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)ና ለዚሁ ዓመት የታደሰ የአቅራቢነት ምዝገባ ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትና የየካቲት ወር ቫት ሪፖርት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ / ስፔስፊኬሽን/ እንዲሁም የጨረታ መገምገሚያ ዘዴ ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይቻላል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በመ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 12 የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ/ ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከፋይናንሻል ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

5. የንብረቱ ማስረከቢያ ቦታ መቐለ ከተማ በሚገኘው የክልሉ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ባዘጋጀው ንብረት ክፍል ሆኖ ማንኛውም ወጪ በአቅራቢ የሚሸፈን ይሆናል።

6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ጋር የቴክኒካል ፕሮፖዛሉን እና የፋይናንሻል ፕሮፖዛሉን ለየብቻ ኦሪጅናል እና ኮፒ በማለት በፖስታ በማሸግ በትግራይ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ቁጥር 12 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን እና ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርበታል።

7. ተጫራቾች ከላይ ከተ.ቁ 1 የተጠቀሱት ሕጋዊነት ማረጋገጫ ማስረጃዎች በሙሉ፣ ባግባቡ የተሟላ ይዘት ያለው የጨረታ ማቅረቢያ ደብዳቤ /letter of Bid/ እና የጨረታ ዋስትና ከቴክኒካል ፕሮፖዛል ኦሪጅናል ጋር አብሮ በፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፤

8. ጨረታው ሚያዝያ ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እነዚህ አካላት የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም።

9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በመ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 12 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 034 440 9971 በመላክ ወይም በሞባይል ስልክ ቁጥር 034 440 3663/ 09 14- 00 42 37ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የትግራይ ክልል የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo