የትግራይ ልማት ማሕበር |FRS እንዲሁም IPSAS ለመተግበር ብቁ አማካሪዎች በጨረታ በማወዳደር አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል፡፡ በዚሁም መሰረት ተጫራቾች፡-

የትግራይ ልምዓት ማሕበር

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የትግራይ ልማት ማሕበር |FRS እንዲሁም IPSAS ለመተግበር ብቁ አማካሪዎች በጨረታ በማወዳደር አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል፡፡ በዚሁም መሰረት ተጫራቾች፡-

1. በዘርፉ የ2017 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የስራ ግብር የከፈሉ፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Trade identification Number /TIN) ያላቸው፣

3. አግባብነት ያለው የአቅራቢነት የምዝገባ ሰርትፊኬት ማቅረብ የሚችሉ

4. ተጨራቾች ለጨረታ ማስከበርያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቀ ባንክ 10,000.00 ብር (አስር ሺ ብር) በ CPO ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5. ተጫራቾች ውል ከታሰረበት ጀምሮ ስራን በ90 (ዘጠና) ተከታታይ ቀናት አጠናቅቀው ማስረከብ የምችሉ፣

6. የጨረታው ሰነድ ከመጋቢት 03/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 17/2017 ዓ.ም የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መቐለ በሚገኘው የትግራይ ልማት ማሕበር ፅሕፈት ቤት ቢሮ ቁጥር 150 ወይም አዲስ አበባ ቦሌ መድሃኔ አለም ፊት ለፊት 7ኛ ፎቅ የሚገኘው ህድሞና ህንፃ ቢሮ ቁጥር 04 መውሰድ ይችላሉ፡፡

7. የጨረታው ሰነድ በተጨራቾች መመርያ መሰረት ተመልቶ፣ ለቴክኒክና ፋይናንሻል ዶክመንቶች ለእያንዳንዳቸው አንድ ኦርጂናልና ሁለት ኮፒዎች በፖስታ ታሽገው በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በመክተት በሚታይ ቀለም ኦርጂናልና ኮፒ በሚል ፅፈው በሁሉም ዶክመንት (አጠቃላይ ላይ ተፈርሞበትና ህጋዊ የሆነ ማህተም በማሳረፍ እስከ መጋቢት 17/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በትግራይ ልማት ማህበር ዋናው ፅሕፈት ቤት ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ CPO ለብቻው ወይም ታሽጎ አልያም ከኦርጂናል ቴክኒካል ዶክመንት ጋር ተያይዞ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ወደ ሳጥን መግባት ኣለበት፡፡

8. ጨረታው ተጨራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባሉበት በ17/07/2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 መቐለ የሚገኘው ዋና ፅሕፈት ቤት ይከፈታል፡፡

9. ፅሕፈት ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታ አይገደድም፡፡

10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 14 74 96 77/ 09 14 70 41 24 መቐለ፣ 09 11 85 94 78 ኢአ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo