ጉዳዩ፦የካፍተርያ ኣገልግሎት ግዥ ግልጽ-ጨረታ ማቅረብ ይመለከታል።
ጽ/ቤታችን ለውስጥ ሰራተኞች እና ለሌሎች ድንበኞች ኣገልግሎት የሚውል ቁርሰ-ቤት ለመክፈት ስለፈለግን ከታች ዘርዝረን ባቀረብናቸው ሜኖ መሠረት ትክክለኛ ዋጋ በመሙላት ጠቅሳችሁ እንድታቀርቡ እንጋብዛለን፡፡
በዚህ መሰረት፦
1. ተወዳዳሪዎች የማወዳደርያ ሰነዳችሁን ከ20/06/17ዓ.ም እስከ 28/06/17ዓ.ም ባለው ግዜ በተካታተይ የስራ ቀናት ውስጥ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባችዎል።
2. ጨረታው ልክ በዛን ዕለት 4:00 ስዓት ተዘግቶ 4:30 ይከፈታል።
3. ይህ ጨረታ በጽ/ቤታችንና በአቅራቢው ድርጅት መካከል እንደ ህጋዊ ውል ሆኖ ያገለግላል።
4. ተወዳዳሪዎች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
5. የግብር ከፋይ መሆኑ Tin/ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችል።
6. አሸናፊው ድርጅት በ7 ቀናት ውስጥ ስራውን አጠናቆ ማስጀመር ይጠበቅበታል።
7. በድርጁቱ በቂ ማተርያል ሳይኖረው እንዲሁም በቂ የሰው ሃይል እና ለስራው የሚያገለግሉ ማተርያሎች ሳይኖረው አሸናፊ ከሆነ በስራችን ለሚደርሰው መሰተጓጎል ተጠያቂ ይሆናል።
8. ኣሸናፊው ድርጅት የኣከባቢው ንፅህና የሚጠብቅ፤ለተገልጋዮች ሆነ ለድንበኞቻችን በጥራትና በጽፈት ደረጃው የጠበቅ ምግብ እና መጠጥ ማቅረብ የሚችል።
9. በአሞላልላይ የሚደርሰው ማንኛውም ስርዝ ድልዝ /ሌላ ግልፅ ያልሆነ ነገር ተቀባይነት የለውም።
10. የውሃ እና የኤሌትሪክ ውጪ ጽ/ቤቱ የሚሸፍነው ይሆናል፡፡
11. የጨረታ ማሰከበርያ (CPO) 5000 ብር በማስያዝ ከጽ/ቤቱ ግዥና ንብረት ሂሳብ መዝጋብ ክፍል የማይመለስ 100 ብር በመክፈል ጨረታ ሰነድ መወሰድ ይችላሉ።
12. ኣሸናፊ ድርጅት ለውስጥ ሠራተኞች ከሚኖ ውጭ ሆነ ከዝርዝር ዋጋ ውጭ መሽጥ፤ለሎች ኣላስፈላጊ የሚረብሽ ድምጽ መስማት፣ ኣልኮል ወይም ሲጋራ መሽጥ ኣይፈቀድም፤በውል ስምምነት እና በመምራያው እና ሕግ ደንብ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል።
13. ኣስተዳደሩ የተሻለ ኣማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።