የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የመቀሌ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የተለያዩ አገልግሎቶች እና ዕቃዎችን ብቃትና ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

ጉምሩክ ኮሚሽን መቐለ ቅ/ጽ/ቤት

የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስታወቂያ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏

የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ቁጥር፦ ECCMB/NCB/002/2017

1 የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የመቀሌ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ከነዚህ በታች የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች እና ዕቃዎችን ብቃትና ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

2. ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ በመንግሥት ግዥ አዋጅ እና መመሪያ በተገለጸው ብሄራዊ ግልጽ ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ሥነ-ሥርዓት መሠረት የሚገዛቸዉ አገልግሎቶች እና ዕቃዎች እንዲሁም በእያንዳንዱ የኣገልግሎትና ዕቃ የሚፈለግ የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የኣገልግሎትና የዕቃ ሎት ቁጥሮች መሰረት በማድረግ ነዉ።

  • ሎት 01 – ለፅሕፈት መሳሪያዎች የሚያስፈልገዉ የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስከበሪያ መጠን ብር 50,000.00
  • ሎት 02 - ለጽዳት ዕቃዎች የሚያስፈልገዉ የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስከበሪያ መጠን ብር 50,000.00
  • ሎት 03 - ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የሚያስፈልገዉ የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስከበሪያ መጠን ብር 60,000.00
  • ሎት 04 - ለፈርኒቸር ዕቃዎች የሚያስፈልገዉ የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስከበሪያ መጠን ብር 40,000.00
  • ሎት 05 - ለቢሮ መጋረጃ እና መስቀያዉ የሚያስፈልገዉ የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስከበሪያ መጠን ብር 30/000.00 /
  • ሎት 06 - ለደንብ ልብስ የሚያስፈልገዉ የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስከበሪያ መጠን ብር 60,000.00
  • ሎት 07- ለህትመት አገልግሎቶች የሚያስፈልገዉ የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስከበሪያ መጠን ብር 10,000.00
  • ሎት 08- ለጥገና ኣገልግሎቶት / የIT እቃዎች እና ኦፊስ ሜሽኖችእና ሌሎች የሚያስፈልገዉ የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስከበሪያ መጠን ብር 10,000.00
  • ሎት 09 ለጥገና ኣገልግሎቶት /የፈርኒቸሮች እና ሌሎች/ የሚያስፈልገዉ የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስከበሪያ መጠን ብር 10.000.00
  • ሎት 10 - ለደረቅ ጭነት ኣገልግሎት የሚያስፈልገዉ የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስከበሪያ መጠን ብር 20.000.00
  • ሎት 11- ለመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች የሚያስፈልገዉ የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስከበሪያ መጠን ብር 50,000.00
  • ሎት 12 - በቦቴ የውሃ አቅርቦት ኪራይ የሚያስፈልገዉየጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስከበሪያ መጠን ብር 10,000.00

3. የግዥ ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ የሚከናወነው ብቁ ከሆነ ተጫራች እና ከአገልግሎቱ እና ከዕቃዎች ጋር አግባብነት ያላቸው የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው፤ የዘመኑ ግብር መክፈላቸውን የሚገልጽ ታክስ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ በመስከረም ወር 2017 ዓ.ም ዲክለር ያደረጉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ በአቅራቢነት የተመዘገበ መሆኑን ማስረጃ የሚያቀርብ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርትፍኬት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።

4. ተጫራቾች በዚህ ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ለመሳተፍ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ከፍለው የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ሰነዱን ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ በአካል በመገኘት መውሰድ ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 በተገለጸው አድራሻ የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስታወቂያ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ህዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30 ላይ ይከፈታል።

6 ተጫራቾች በጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው ለመሳተፍ የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስከበሪያ መጠን ከላይ በተራ ቁጥር 2 በተገለጸው ለእያንዳንዱ የሎት ምድብ የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

7. የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ሰነድ የሚገባበት አድራሻ ትራንስ ኢትዮጵያ ኣጠገብ የሚገኘው የዉሃንስ ግደይ ህንጻ ጉምሩክ ኮሚሽን መቐለ ቅርንጫፍ ፅሕፈት ቤት 3ኛ ፎቅ ሃብት አስተዳዳር ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 በተዘጋጀዉ የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ሳጥን ይሆናል።

8. ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ የተሻለ ኣማራጭ ካገኘ ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 14 830 469 / 09 19 068 385 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል።

ጉምሩክ ኮሚሽን የመቐለ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo