የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ የተለያዩ የማስተማሪያ መፃህፍት በጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል ስለዚህ በዚህ ጨረታ ለመወዳደር የሚፈልግ

የትግራይ ትምህርቲ ቢሮ

1 ሕጋዊ የሕትመት ንግድ ፍቃድ ያለዉና የ2008 ዓ/ም ንግድ ፍቃድ ያሳደሰ

2 በተጨማሪ እሴት ታክስና አቅራቢነት የተመዘገበ ቲን ቁጥር ያለዉና ለሁለም ማስረጃ የሚቀርብ የየካቲት 2008 ቫት ዲክለረሸን የሚቀርብ

3 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 75,000 የመንግስት ግዢ መመሪያ በሚፈቅደዉ መሰረት የሚቀርበ

4 ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምረሮ ለተካታታይ 15 ቀናቶች መቐለ ከሚገኘዉ ከትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ህንፃ 1ኛዉ ፎቅ ግዢ ክፍል የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50 በመክፈል መዉሰድ ይቻለል

5 የጨረታ አሸናፈዉ ዉል ከፈፀመበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 15/2008 ዓም ትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ መጋዝን የሚያስረከብ መሆን አለበት

6 ተጫራቾች የጨረታዉን ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በተከታታይ እስከ 15ኛዉ ቀን 8:00 ሰዓት ድረስ በትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ 1ኛዉ ፎቅ ግዢ ክፍል የጨረታ ደኩመንት ማስገባት ይቻላል

7 ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንት ፋይናንስ ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻዉ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ለባቸዉ

8 ጨረታዉ በ15ኛዉ ቀን በ8:45 ሰዓት ታሽጎ በ9:00 ሰዓት ይከፈታል 15ኛዉ ቀን በዓል ከዋለ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ቀን የመዝጊያነና የመክፈቻ ቀን ይሆናል

9 ቢሮዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ

10 ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቀጥር 0344 40 34 77/ 408299 መጠየቅ ይቻላል

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo