የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
ቁጥር 03/2017
በመቐለ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት እና በመቅረጫ ጣቢያዎች ስር ተይዘውና ተወርሰው የሚገኙ
- የተለያዩ የምግብ ነክ ዕቃዎች፣
- የኮንስትራክሽን ዕቃዎች፣
- የንፅህና ዕቃዎች፣
- የቤትና የቢሮ ዕቃዎች እና
- ልዩ ልዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ ሁኔታ እና መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ለጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጡ ዕቃዎች ጋር ተዛማጅነት ያለው ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢው መ /ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የግልጽ ጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በጽ/ቤታችን የዕለት ገቢ ሰብሳቢ ቢሮ ቁጥር 104 በመገኘት ይህ ጨረታ አየር ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ መዝጊያው ቀን ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- በጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ከሚሰጡት ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና CPO በመቐለ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚካሄደው በመቐለ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሲሆን በማስታወቂያው በተገለፀው ጊዜ እና ቦታ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሰነዱ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እስከ 7ኛ ቀን ድረስ ለጨረታ የቀረቡ የዕቃዎች ናሙና በቅ/ጽ/ቤቱ ውርስ መጋዘን በአካል በመሄድ ማየት የሚቻል ሲሆን እንዲሁም የኮንስትራክሽን ዕቃዎች ራማ ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ በአካል በመሄድ መመልከት ይቻላል።
- ጨረታው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከረፋዱ 4፡00 (አራት ሰዓት) ተዘግቶ 4፡30 (አራት ከሰላሳ ደቂቃ) ይከፈታል፡፡
- ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለጸው ጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 8ኛው ቀን የሥራ ቀን ሳይሆን ቢቀር የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
- በጨረታው አሸናፊ ለሆኑ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲፒኦ ከከፈሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸነፉት ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀ ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን መረከብ አለባቸው፡፡
- ከላይ በተራ ቁጥር 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ ለጽ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 34 240 7107 ወይም በስልክ ቁጥር +251 34 240 8513 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በጉምሩክ ኮሚሽን መቐለ ቅ/ጽ/ቤት