ኢማጅን ዋን ዴይ ኢንተርናሽናል ኦርጋናይዜሽን /imagine1day/በትምህርት ጥራት ማሻሻል ሥራ ላይ የተሰማራ ሲሆን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን እቃዎች በ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

ኢማጅን ዋን ደይ

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ኢማጅን ዋን ዴይ ኢንተርናሽናል ኦርጋናይዜሽን /imagine1day/ የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ የውጭ በጎ አድራጎት ድርጅት በኦሮሚያ፣ አማራ፣ትግራይ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፣ አፋር ክልል እና በደቡብ ክልል በትምህርት ጥራት ማሻሻል ሥራ ላይ የተሰማራ ሲሆን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን እቃዎች በ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

ተ/ቁየእቃው አይነትብዛትሎትፕሮጀክት
1የተማሪዎች መቀመጫ ዴስክ (combined desk)320IHilari & Galen
2የተማሪዎች መቀመጫ ዴስክ (combined desk)200IIEHF

ስለሆነም

➢ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉበት እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

➢ የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO ለ30 · የሚቆይ ከሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ከቫት ውጭ 2% ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስያዝ የሚችሉ

ስለጨረታው የሚገልፀውን ሰነድ የማይመለስ ብር ለአንድ ሎት 200.00 (ሁለት መቶ ብር) እና የታደሰ ንግድ ፈቃዳቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል

➢ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን መቀሌ ከተማ ከሚገኘው ዋና መስሪያቤት ከግንቦተ 26 2016 እስከ እስከ ሰኔ 4 2016 ዓ/ም ባለው የስራ ሰዓት የጨረታ ዶክመንቶችን መግዛት ይችላሉ፡፡

➢ የሚወዳደሩበትን ዋጋ የድርጅቱን ማህተም ባለዉ ኢንቨሎፕ አንድ ኮፒ እና አንድ ኦርጂናል በማድረግ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዎስትና ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ሰኔ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ከ 9፡00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል

➢ ተጫራቾች ሁሉ ከዚህ ደብዳቤ ጋር የተያያዘውን ዝርዝር ዕቃዎች ዋጋ በመሙላት ጨረታው ሰኔ 5 ቀን 2016 ዓ.ም 9፡00 ሰዓት ላይ ራሳቸው ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው (በሰንዶች ማረጋገጫ የተረጋገጠ ህጋዊ ውክልና የያዙ ወኪሎቻቸው) መቀሌ ከተማ አዲ ሃዉሲ ከዋናዉ አስፓልት ከሊባኖስ

ሆቴል 200ሜትር ወደ ዉስጥ ገባ ብሎ

የድርጅቱ ዋና ፅሕፈት ቤት ጨረታው ይከፈታል::

➢ በድርጅት የውክልና ዳብዳቤ እንደማንቀበል በትህትና እንገልጻልን

➢ ድርጅቱ ለተሻለ ኣማራጭ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ:-ኢማጂን ዋን ደይ ኢንተርናሽናል ኦርጋናይዜሽን(መቀሌ)

የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0900309103/0914141190/0911363401

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo