መስሪያ ቤታችን ከዚህ ደብዳቤ ጋር ኣባሪ በተደረገው ሠንጠረዥ ውስጥ የተጠቀሱት ዕቃዎች መግዛት ሰለሚፈልግ የመወዳደሪያ ሀሳብ እንድታቀርቡ ይጋብዛል፡፡

ቢሮ ሕርሻን ገጠር ልምዓትን

ፕሮፎርማ ቁጥር 141 /2016

ጉዳዩ፡- ለዕቃዎች ግዥ የመወዳደርያ ሀሳብ እንድያቀርቡ ስለመጠየቅ

መስሪያ ቤታችን ከዚህ ደብዳቤ ጋር ኣባሪ በተደረገው ሠንጠረዥ ውስጥ የተጠቀሱት ዕቃዎች መግዛት ሰለሚፈልግ የመወዳደሪያ ሀሳብ እንድታቀርቡ ይጋብዛል፡፡ መስሪያ ቤታችን ግዢውን የሚፈፅመው በጥራትም ሆነ በዋጋ ብቁ መሆናቸውን አረጋግጦ የመረጣቸውን ይሆናል፡፡

1. የተፈላጊ ዕቃዎች ዝርዝር ኣባሪ በተደረገው ሠንጠረዥ ላይ ተመልክተዋል፡፡

2. ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ለመሳተፍ የሚያስችላቹ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TI/፣ ለቫትተመዝጋቢዎች የቫት ምዝገባ ሰርቲፊኬትና ያለፈውን ወር ቫት ዲክሌር የተደረገበት ማስረጃ ፣ በመንግስት

ግዢ ለመሳተፍ የተሰጠ ፍቃድ ማሰረጃዎች ፎቶ ኮፒ መያያዝ አለበት፡፡

3. የመወዳደርያ ሃሳቡ በታሸገ ኢንቨሎፕ ሆኖ እስከ 19/09/2016 ዓ/ም ጥዋት 4፡00 ሰዓት ለቢሯችን የግዢ ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 መድረስ _ አለበት፡፡ፕሮፎርማው/የመወዳደርያ : ሃሳቡ/ በ 19/09/2016 ዓ/ም ጥዋት 4፡00 ተዝግቶ 4፡30 ይከፈታል፡፡

4. አሸናፊ አቅራቢ የሚለየው ለተጠየቁት ጠቅላላ እቃዎች በሙሉ በድምሩ( Lot) ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል፡፡ በዚህ መስፈርት መሰረት ለሁሉም ዕቃዎች ዝርዝር ዋጋ ያላቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡

5. የእቃው ማስረከብያ ቦታ በቢሯችን በሚገኘው ንብረት ክፍል ሆኖ ማስረከብያ ግዜው ግዢው ከታዘዘበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡

6. የፕሮፎርማው ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ጊዜ አንስቶ ለ 15 ቀናት ይሆናል፡፡

7. አቅራቢዎች በእያንዳንዱ የዕቃ ዝርዝር ማቅረብያ ሰንጠረዥ ውስጥ የዕቃው ዓይነትና ብዛት፣ነጠላ ዋጋ፣እና ጠቅላላ ዋጋውን መሙላት እንዲሁም ቀን ፣ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም ማሰፈር ይገባቸዋል፡፡ የመወዳደርያ ሃሳቡ ዋጋ የሚቀርበው በኢትዮዽያ ብር ይሆናል፡፡

8. ለአሸናፊ ተወዳዳሪ ዕቃውን ሙሉ ለሙሉ በውሉ መሰረት አጠናቆ ማስገባቱና ጥራቱ ከተረጋገጠ በኃላ በሰባት ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያ ይከፈለዋል።

9. ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ታክስን የሚያካትትና የማያካትት መሆኑ መግለፅ አለባቸው፤ታክስ ካልተገለፀ የቀረበው ዋጋ ታክስ እንዳካተተ ተቆጥሮ ውድድሩ ይካሄዳል።


10. አሸናፊ ተወዳዳሪዎች ደብዳቤ ከደረሳቸው በኋላ በሶስት/ 3/ የስራ ቀናት ውስጥ 10 % የጠቅላላ ኮንትራክት የውል ማስከበርያ በመስራቤታችን ስም CPO አሰርተው ውል ማሰር የሚችሉ ብቻ መሆን አለባቸው፡፡

11. ግዢ ፈፃሚው መስራቤት ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት የዕቃውን ጠቅላላ ብዛት እስከ 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት)ጨምሮ ወይም ቀንሶ መፈራረም ይችላል፡፡

12. ማንኛውም ተሳታፊ ከፕሮፎርማ መዝግያ ቀንና ሰዓት በፊት ቴክኒካልና ፋይናንሻል በአንድ ኢንቨሎፕ

በማሸግ ኦርጅናል ሰነዶችን የመወዳደርያ ሃሳብ/ ማቅረብ ይኖርበታል ፡፡ ከፕሮፎርማው መዝግያ ቀንና ሰዓት ሰዓት በኃላ የቀረበ ሰነድ /የማወዳደርያ ሃሳብ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን ኢንቨሎፑ ሳይከፈት ለተወዳዳሪው ተመላሽ ይሆናል፡፡

13. የቴክኒክ መስፈርቱን/ ዝርዝር መግለጫውን/ ካሟሎት አቅራቢዎች መካከል የተስተካከለ ዝቅተኛ ዋጋ ላቀረበው ተጫራች ኣሸናፊ ይደረጋል፡፡

14. መስርያ ቤታችን ፕሮፎርማው በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo