በመቐለ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ፅ/ቤት ስር የተተውና በኮንትሮባንድ ተውርሰው የሚገኙ የተለያዩ የምግብ ነክ ዕቃዎች፣ ኣልባሳትና ጫማዎች የንጽህና እቃዎቸ፣ ኣልክትሮኒክስ እቃዎቸ የቤትና የቢሮ እቃዎቸ እና ሎይሎች ልዩ ልዩ እቃዎቸ ባሉበት ሁኔታ ብሓራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሽጥ ይፈልጋል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽን መቐለ ቅ/ጽ/ቤት


በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን መቐለ ቅ/ጽ/ቤት
የተወረሱ ንብረቶች ሽያጭ ማስታወቂያ- ቁጥር 05/2016

በመቐለ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ፅ/ቤት ስር የተተውና በኮንትሮባንድ ተውርሰው የሚገኙ የተለያዩ የምግብ ነክ ዕቃዎች፣ ኣልባሳትና ጫማዎች የንጽህና እቃዎቸ፣ ኣልክትሮኒክስ እቃዎቸ የቤትና የቢሮ እቃዎቸ እና ሎይሎች ልዩ ልዩ እቃዎቸ ባሉበት ሁኔታ ብሓራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሽጥ ይፈልጋል፡፡

1) በመሆኑ ቅ/ፅ/ቤቱ ባወጣው የዕቃ ሽያጭ ጨረታ ወዳደር የሚፈልግ ማንኛው ተጫራች ፦

ሀ) በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርቲፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡

ለ) የዚህ አንቀፅ ፊደል ተራ (ሀ) ድንጋጌ ቢኖርም ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች ግምታዊ ዋጋቸው 500,000 (ከአምስት መቶ ሺ ብር) በታች ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርቲፊኬት ማቅረብ አይገደድም፡፡

2) ተጫራቾች የሓራጅ ጨረታ ሰነድ ከሰኞ ሚያዝያ 14 ቀን 2016ዓ/ም ጀምሮ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት፤ የጨረታ ሰነዱ መግዛት ይችላሉ፡፡

3) በሃራጅ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ለምግብ ነክ ብር 30000 እንዲሁም ለሌሎች ዘርፍ የዕቃውን የጨረታ መነሻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና CPO በመቐለ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማስያዝ ይኖሩበታል፡፡

4) ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ፡፡

የቅ/ጽ/ቤቱ ስምየንብረቱ ዓይነትጨረታው ዓይነትየንብረት መመልከቻ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮየጨረታው መክፈቻ ቀን ና ሰዓት
እስከ
መቐለ ጉ/ቅ/ጽ/ቤትየተለያዩ ዓይነት ንብረቶችሃራጅ ጨረታ14/08/2016 ጀምሮ22/08/16 ከቀኑ 6፡0022/08/2016ዓ.ም ከቀኑ ከ8፡00 ጀምሮ ይካሄዳል

5) የጨረታ መክፈቻ ቦታ መቐለ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ

ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡

6) ለጨረታ አሸናፊዎች ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋስትና በ3 ቀናት ወስጥ ተመላሽ ይደረግላችዋል::

7) የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ለማሸነፉ ከተገለጸለት ጊዜ ጀምሮ 5(አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፈበት ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት::

8) ከላይ በተ/ቁ 7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡

9) ቅ/ፅ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ሊሰርዝ ይችላል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን መቐለ መቐለ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት +251342407107 ወይም +251342408513/ በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑ እንገልፃለን


ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo