በትግራይ ክልል ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ዘላቂ የመሬት አያያዝ ፕሮግራም /RLLP/ Resilient Landscapes and Livelihood Project በአለም ባንክ ከሚደገፉ ፕሮጀክቶች ይህ ወረዳ አንዱ ሲሆን በ 2016 ዓ.ም በፀደቀውን የግዥ ዕቅድ መሰረት በትግራይ ዘላቂ የመሬት አያያዝ ፕሮግራም ስር ላሉ ፕሮጀክት ወረዳዎች አገልግሎት የሚውል የ45 ቀን እድሜ ያላቸው ደሮዎች/45 day old chickens ግዥ በ Request for quotation (RFQ) አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

የኣፅቢ ወንበርታ ወረዳ እቅድና ፋይናንስ ጽህፈት ቤት

ጉዳዩ፡- የ45 day old chicken (የ45 ቀን እድሜ ያላቸው ደሮዎች) ግዥ መሸጫ ዋጋ እንድያቀርቡ ስለመጠየቅ

በትግራይ ክልል ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ዘላቂ የመሬት አያያዝ ፕሮግራም /RLLP/ Resilient Landscapes and Livelihood Project በአለም ባንክ ከሚደገፉ ፕሮጀክቶች ይህ ወረዳ አንዱ ሲሆን በ 2016 ዓ.ም በፀደቀውን የግዥ ዕቅድ መሰረት በትግራይ ዘላቂ የመሬት አያያዝ ፕሮግራም ስር ላሉ ፕሮጀክት ወረዳዎች አገልግሎት የሚውል የ45 ቀን እድሜ ያላቸው ደሮዎች/45 day old chickens ግዥ በ Request for quotation (RFQ) አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤ በዚሁ መሰረት ከዚህ ደብዳቤ ጋር አባሪ በተደረገው ሠንጠረዥ ውስጥ የተጠቀሱት ደሮዎች የሚደርስበት ልዩ ተፋሰስ ወረዳ ስም በሰባት ቀበሌዎች

የተዘረዘሩ ቦታ ድረስ ሲሆን ጠቅላላ የእቃው መሸጫ ( የትራንስፖርት መጓጓዣ : መጫኛና ማውረጃ ) ያካተተ ዋጋ በታሸገ ፖስታ እንድትሰጡን እንጠይቃለን፡፡

ማብራሪያ፤

1. የመወዳደርያ ሃሳቡ በታሸገ ኢነቨሎፕ ዉስጥ ሆኖ እስከ 19/07/2016 ዓ/ም 5:00 ሰኣት ለግዢ ፈፃሚዉ መስራቤት ወረዳ ኣፅቢ እቅድና ፋይናንስ መድረስ ኣለበት፡፡ የመወዳደርያ ሃሳቡ በ 19/07/2016 ዓ/ም 5:30 ሰኣት ይከፈታል፡፡

2. ተጫራቶች ጭረታ ሰነድ ከኣፅቢ እቅድና ፋይናንስ መስራቤት በስራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 6፡00 ከስዓት በፊት እና ከ8፡00 እስከ 11፡00 ባለዉ ግዜ በኣካል ተገኝቶዉ ሰነድ ጨረታውን መዉሰድ ይገባቸዋል፡፡

3. የጨረታ ማስከበርያ 10,000.00 ብር ማስያዝ የሚችል

4. የሚሰጡት ጠቅላላ ዋጋውን በቁጥሮና በፊደል መጻፍ አለባቸው :: በቁጥርና በፊደል በተገለፀው የዋጋ መጠን መካከል አለመጣጣም ካለ በፊደል የተገለፀው ተቀባይነት ይኖረዋል :: በነጠላ ዋጋ እና በጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ ነጠላ ዋጋው ተቀባይነት ይኖረዋል ።

5. በዕቃ ዝርዝር ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ውስጥ የዕቃውን አይነትና ብዛት ፤ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋውን መሙላት እንዲሁም ቀን ፣ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም ማስፈር ይገባቸዋል ::

6. የሚሰጡት ዋጋ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ዋጋውን ከሰጡበት ጊዜ ጀምሮ ለ 15 ቀናት የሚጸና ይሆናል፡፡

7. የደሮዎች ማስረከቢያ ቦታ አፅቢ ወረዳ ልዩ የተፋሰስ ወረዳ ስም በሊጋ፤ ዒንደሎት ፤ድባብ ዓኮሬን፤ ዓዶ ኮማ ሓየሎም ፤ሚካኣኤል ኣምባና ባርካ ዓዲ ስብሓ ሁኖ የግዥ ትዕዛዝ ከተሰጠበት ወይም ውስጥ ይሆናል፡፡

8. ለገበሬ የሚቀርቡ ደሮዎች እድሚያቸው 45 ቀን መሆን

9. የደሮዎች ዝርያቸው የተሻሻለ ሆኖ ጥምር (Dul) የስጋና ትመስላል ዝርያ

10. ደሮ የሚያቀርብ አሳዳጊ (Out grower) የአንድ ቀን ጫጭት ከኢትዮ ችክን (Ethio-chicken) ወስዶ በከተማ ኣፅቢ እንዳስላሴ የሚያሳድግ መሆን ኣለበት፤

11. ጫጭቶቹ 45 ቀን እስኪሞላቸው በወረዳውና በወረዳ ባለሞያዎች ክትትል እየተደረገላቸው ተገቢ ክትባት ፡ ህክምና የተመጣጠነ ምግብ ፣ ወዘተ አግኝቶ ማደግ አለባቸው "

12. አንድ ደሮ ኣቅራቢ 45 የሞላቸው ደሮዎች በተመረጡ ቀበሌዎች ወስዶ የወረዳው የቀበሌው ባለሞያ ያስረክባል። ደሮዎቹ በአርሶ አደሩ እጅ እስኪገቡ የሚያጋጥም የሞት የመታመም ወይም ሌላ አደጋ ኪሳራው የአቅራቢው ይሆናል። እንዴ አጋጣሚ ለደረሰ የዴሮዎቹ ጉዳት ሞት እንዲተካ ይደረጋል፤

13. 45 ቀን እድሜ የሞላቸው ደሮዎች በአማካይ ከ380 - 450 ግራም መሆን ይኖርባቸዋል ፣

14. ውል ተቀባይ ደሮዎች ሙሉ ለሙሉ በውለታ መሰረት አጠናቆ ማስገባቱና ማጠናቀቁ ከተረጋገጠ በኋላ ቢበዛ በ 10 ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያ የሚይፈፀም ይሆናል ።

15. የሚሰጡት ዋጋ በኢትዮጵያ ብር ይሆናል ።

16. ውል ተቀባይ የቅድሚያ ክፍያ እንዲሰጠው ከጠየቀ የግዥ ፈፃሚ ኣካል ከውሉ ከ 20 % ያልበለጠ ሊከፍለው ይችላል ይሁን እንጂ ይህ ተግባራዊ የሚሆነው ውል ተቀባዩ ከታወቀ ባንክ የተሰጠ ከሚቀበለው የቅድሚያ ክፍያ እኩል የሆነ ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ለግዥ ፈፃሚ አካል ማቅረብ የሚችል ከሆነ ብቻ ተፈፃሚነት ይሆናል ።

17. ደሮ የሚያቀርብ አሳዳጊ (Out grower)

➢ የአንድ ቀን ጫጭት ከኢትዮ ችክን (Ethio-chicken) ወስዶ የሚያሳድግ ይሆናል ፣

➢ ጫጪት ቀለብና መድሃኒት በፓኬጅ ከኢትዮ ችክን የሚወስድና ማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ የሚችል ፤

➢ ለሚያቀርባቸው ደሮዎች የሚያሳድግበት በቂ ማሳደግያ ክፍል ያለው መሆን ይኖርበታል ፣

➢ የደረዎቹ አያያዝ አመጋገብ፣ ጤና፣ እንክብካቤ፣ ወዘተ የተሟላ የየእለቱ አጠቃላይ ማህደር ሪከርድ ማቅረብ የሚችል

➢ ፋርሙ ባዮሴኩሪቲ ያለውና በተሟላ የሚያስፈፅም መሆን ይኖርበታል

18. አሸናፊው አቅራቢ የሚለየው ለእያንዳንዱ ዕቃ ያቀረበው Item by Item / ዝቅተኛ ዋጋ መሰረት ይሆናል

19. ግዢ ፈፃሚው መቤት ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውለታ ከመፈረሙ በፊት የዕቃውን ጠቅላላ ብዛት እስከ 20% (ፐርሰንት) ጨምሮ ወይም ቀንሶ መፈረም ትችላል።

20. የሚከተሉት ሰነዶች ከ ሰነዱ ጋር ማያያዥ ይኖርባቸዋል ::

➢ የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ከትግራይ ክልል ግብርና ወይም ከኣፅቢ ዘፈር ቁጠባ | እንስሳት ልማት ሃብት ስራ

ሂደት የሚያቀርብ

➢ የተጫራቹን የስራ ዘርፍ የሚያሳይ የ2016 የታደሰ ንግድ ፈቃድ

➢ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር

➢ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርቲፊኬት ከ

➢ የጥር ወር ቫት ዲክለሬሽን ያደረገ

➢ የሚመለት ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን A ሰነዱ በኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ኣለበት?

➢ ስም ና ኣድራሻ በፖስታ ከታሸገ ብኋላ መገበው

ኣባሪ 1. የደሮ ዓይነት ፣ መጠን ፣ የሚሰጡት ዋጋ ከነ ትራንስፖርት መሆኑ ታሳቢ ያድርጉት ማለት (ቃ/ኣሚን :ጎ/ናዕለ :ድ/ዓኮሬን፣ፈ/ወይኒ፡ባርካ ዓዲ ስብሓ፣ሓየሎም እና ሚካኤል እምባ) ማእከል

ተ.የዕቃዎች ዝርዝርኣድራሻመለኪያብዛትየያንዱ ዋጋ (ብር)ጠቅላላ ዋጋ (ብር)
1የ45 ቀን እድሜ ያላቸው ደሮዎች/45-day old chicken/ኣዕቢቁፅሪ2200
2ኣጉላዕቁፅሪ4000
ጠቅላላ ድምር6200

የሚመላው ዋጋ በታች ባለው ስፐስፊኬሽን መሰረት መሞላት አለበት

ይህ ዋጋ የሞላ ስም. _________________


Specification for Chickens

የዕቃዎች ዝርዝርደሮ የሚያቀርብ አሳዳጊ (Out grower)
የ45 ቀን እድሜ ያላቸው ደሮዎች/45- day old chicken➢ የአንድ ቀን ጫጭት ከኢትዮ ችክን (Ethio-chicken) ወስዶ የሚያሳድግ ይሆናል ፣
a. ጫጪት ፣ ቀለብና መድሃኒት በፓኬጅ ከኢትዮ ችክን የሚወስድና ማረጋገጫ
ሰነድ ማቅረብ የሚችል ፣
b ደሮዎች 45 ቀናት የሚያድጉ በወረዳው ውስጥ መሆን ኣለበት ፡
c. ለሚያቀርባቸው ደሮዎች የሚያሳድግበት በቂ ማሳደግያ ክፍል ያለው መሆን ይኖርበታል !
d. የደረዎቹ አያያዝ ፣ አመጋገብ ፣ ጤና ፣ እንክብካቤ ፣ ወዘተ የተሟላ የየእለቱ አጠቃላይ ማህደር ሪከርድ ማቅረብ የሚችል ፣
e ፋርሙ ባዮሴኩሪቲ ያለውና በተሟላ የሚያስፈፅም መሆን ይኖርበታል
f. ለገበሬ የሚቀርቡ ደሮዎች እድሚያቸው 45 ቀን መሆን አለበት
9. 45 ቀን እድሜ የሞላቸው ደሮዎች በአማካይ ከ 380 - 450 ግራም መሆን ይኖርባቸዋል

ከሰላምታ ጋር

ግልባጭ

➢ለፅ/ቤታችን የገቢ ልማትና ፋይናንስ አስተዳደር ኣፅቢ

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo