የመቀሌ ከተማ እቅድና ፋይናንስ ፅ/ቤት የተለያዩ ኣይነት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ኣወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ።

የመቐለ ከተማ እቅድና ፋይናንስ ጽህፈት ቤት

ለ2ኛ ግዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቅ

የመቀሌ ከተማ እቅድና ፋይናንስ ፅ/ቤት የተለያዩ ኣይነት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ኣወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ። ስለዚህ በዚ ጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ከታች የተዘረዘሩ መስፈርቶች የምታማሉ ተወዳዳሪዎች ጨረታ ሰነድ ከፅ/ቤታችን በመውሰድ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል። ተፈላጊ መስፈርቶች

1. የዘመኑ ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣ የኣቅራቢነት ሰርቲፊኬት ፣ የቫት ምዝገባ ሰርቲፊኬት ፣ የቅርብ ወር የቫት ሪፖርት ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ ።

2. የጨረታ ማስከበርያ ብር 100,000.00(ኣንድ መቶ ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (CPO)፣ በጥረ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በፅህፈትቤታችን ስም ማስያዝ ኣለባቸው ።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ሰኣት የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ ።

4. ተጫራቾች ፋይናንሻል የጨረታ ሰነዳቸው ኣንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ።

5. ጨረታ ከ ታህሳስ 12/2016 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 30/2016 ዓ/ም 3:30 ለተጫራቾች ክፍት ሁኖ የሚቆይ ሲሆን በዚህ ቀን 3:30 ተዘግቶ 4:00 ሰዓት ይከፈታል ።

6. ጨረታ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰ ቀን በፅ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 033 ይከፈታል።

7. ተጨራቾች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ገፅ የድርጅት ማህተም እና ፊርማ ማድረግ ኣለባቸው ።

8. ፅህፈት ቤታችን ጨረታ ከተከፈተ በኋላ 20% የመጨመር እና የመቀነስ መብት ኣለው ።

9. ፅህፈት ቤታችን የተሻለ ኣማራጭ ካገኘ ጨረታ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

10. ኣድራሻችን በመቐለ ከተማ ኣግኣዚ ኦፕሬሽን ህንፃ ቢሮ ቁጥር 033 ይገኛል።

11. ለበለጠ ማብራርያ በስራ ሰኣት በኣካል ቀርባችሁ መጠየቅ ይቻላል ።

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo