መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የተለያዩ ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት ምዝገባ) ሰርቲፍኬት ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርትፊኬት እና የአቅራቢ ምዝገባ ሰርትፊኬት ማቅረብ የሚችል፣
2. የቀረበው ዝርዝር የቴክኒክ መስፈርት ማሟላት የሚችል
3. ለጨረታ ማስከበርያ ቢድ ቦንድ በባንክ የተመሰረተ CPO /ሲፒኦ/ ወይም የባንክ ዋስትና በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ስም ማስያዝ የሚችል
ተ.ቁ | ምድብ | የጨረታ አይነት | የጨረታ ማስከበሪያ(ሲፒኦ) |
1 | ሎት1 | የመስተንግዶ አገልግሎት | 50,000.00 |
2 | ሎት2 | ሕትመትና የሕትመት ውጤቶች | 50,000.00 |
4. ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳ/ፅ/ቤት መውሰድ ይችላል።
5. ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣት ቀን ጀምሮ እስክ 15ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የማወዳደርያ ሰነዳቸው ማስገባት ይችላሉ።
6. ጨረታው ከወጣበት በ15ኛው ቀን ጠዋት 3፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን በ4:00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
7. በጨረታው አሸንፎ በወቅቱ ውል ለማያስር የጨረታ አሸናፊ ያስያዘው የጨረታ ማስከበርያ (ቢድ ቦንድ) ወይም CPO አይመለስም።
8. ዩኒቨርሺቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በክፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ ማብራርያ ስልክ 034 441 4784/09 14 72 74 48 ደውሎ ማነጋገር ይችላሉ።