የትግራይ ብሓራዊ ከልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ጀነሬተሮች ፣የተለያዩ ኮምፒተሮችና ተዛማጅ ዕቃዎች፣ የተለያዩ ኤለክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ በዚሁ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ ተጫራቾች ይጋብዛል

ትግራይ ክልል ጤና ቢሮ

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶች

  1.  የዘመኑ የመንገስት ግብር የከፈሉና የዘመኑ ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ
  2.  የግብር ከፋይ ቁጥር መመዝገባቸዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3.  ተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገባቸዉና የ ሕዳር ወር ቫት ዲክለር ማድረጋቸዉማስረጃ የሚያቀርቡ
  4. በአቅራቢዎች ዝርዝር ዉስጥ የተመዘገቡ መሆናቸዉን ማስረጃ የሚያቀርቡ
  5.  የጨረታ ማስከበሪያ

ጀነሬተር ግዥ ብር 50, 000 (አምሳ ሺህ) በሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ

ኮምፒተርና ተዛማጅ ዕቃዎች ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ

ለኤለክትሮኒክስ ጨረታ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ

  1. የጀነሬተርና ኤለክትሮኒክስ ግዥ ጨረታ ለእያንዳንዳቸዉ ቴክኒካል ዶክሜንት አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል ዶክሜንት አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ማቅረብ ግዴታ ሲሆን  ለኮምፒተርና ተዛማጅ ዕቃዎች ደግሞ ፋይናንሻል ዶክሜንት ብቻ የሚቀርብ ሆኖ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን በስራ ሰዓት የቢሮዉ የግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 42 ማስገባት ይጠበቅባቸዋል
  2. ጨረታዉ በአዲስ ዘመንከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጨረታዉ የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀንም ሆነ ሰዓት እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መመሪያዎች በሚሸጠዉ ጨረታ ሰነድ ላይ መመልከት ይቻላል
  3. አሸናፊ ተጫራቾች በራሳቸዉ ማጋጋዣ ሌሎች ወጪዎች በመሸፈን ወደ ትግራይ ጤና ቢሮ መጋዝን ማድረስ ይጠበቅባቸዋል
  4. ጨረታዉ ፀንቶ የሚቆየዉ ለ 60 ቀናት ነዉ
  5. አሸናፊ ተጫረቾች ዉል ካሰሩበት ቀን ጀምሮ ኮምፒተርና ተዘማጅ ዕቃዎች  እና ኤለክትሮኒክስ ጨረታ በ 45 ቀናት ጀነሬተር ግዥ በሦስት ወራት ገቢ እንዲያደርጉ ግዴታ አለባቸዉ
  6.  የጨረታ  ሰነዱ ዋጋ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ብር 50 ከፍለዉ ከትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የግዥ ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 42 በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ
  7.  ቢሮአችን በጨረታዉ 20% መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል
  8.  ቢሮአችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉ በሙሉም ሆነ በከፈሊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ

ለበለጠ መረጃ  0344404717/09 14733312

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo