የአፋር መንገድ ልማት ትራንስፖርት ቢሮ በመንገድ ፈንድ በጀት በሀደሌኤላ አባኬበዳ መንገድ ላይ የመልሶ ግንባታ ስራ መከናወን ስለሚፈልግ በG.C ከደረጃ 5 በላይ የሆኑ የግንባታ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ኣፋር መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ
  • ጨረታዉ በኣዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣበት ቀን : 1/7/2012
    ጨረታዉ የሚዘጋበት ቀን : ለ10 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 10:30
    ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን :  ለ10 ተከታታይ ቀናት 11ኛዉ ሰኣት
    ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ሠመራ በሚገኘው በዋና መ/ቤታችን ግዥ/ፋይ/ንብ/አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፣ 
  • ተጫራቾች ጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ በ2012 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃዳቸውን፣ የቫት ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ የግብር  ከፋይ መለያ ቁጥር ሠርተፍኬት በደረጃ 5 የጠቅላላ ስራ ተቋራጭነት የታደሰ ፈቃድ እንዲሁም የግንባታ የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ እና የመንግስት መ/ቤቶች በሚፈጽሙት ግዥ ለመሳተፍ በአቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ ምስክር ወረቀት አብሮ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና /ቢድቦንድ/ 2% ወይም ከ20ሺህ ብር ያላነሰ ዋጋ ያለው በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒኦ ማስያዝ አለባቸው፣ 
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 10፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ) የአፋር መንገድልማት ትራንስፖርት ቢሮ ግዥ/ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ 
  • ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ለ10 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ  10:30 ሠዓት ሆኖ ወዲያውኑ ሳጥን ታሽጐ በዚያው ቀን 11ኛው ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣ 
  • ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

አድራሻ ፡- ሠመራ ስልክ ቁጥር፡- 033 66600 79 

- የመ.ሳ.ቁ 41 

ፋክስ ቁጥር 033 666 0754 

የአፋር መንገድ ልማት ትራንስፖርት ቢሮ 

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo