ፋብሪካችን ሞሓ የለስላሳ መጠጦች ኢ/ሪ አ ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ይፅህፈት መሳሪያዎች በጨረታ ኣወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

ሞሃ የስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ S,C

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መመርያ  አክብራችሁ የምትፈልጉ ተጫራቾች ሁሉ መጫረት የምትችሉ መሆኑ በአክብሮት እንገልፃላን

የጨረታ መመሪያ

1 የዚህ ጨረታ አላማ የፋብሪካችን የ 6 ወር ፍጀታ የሚዉል የፅህፈት መሳርያዎች አወዳድሮ ለመግዛት ነዉ

2 ተጫራቾች በፅህፈት መሳሪያ ኣቅራቢነት ተመዝግቦ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ እና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆናቸዉ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል

3 ተጫራቾች ለጨረታዉ /ማስከበሪያ 5000 ብር በCPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ወይም በሚከፈትበት ማስያዝ ይኖርባቸዋል በጥሬ ገንዘብ የሚመጣ ተቀባይነት ኣይኖረዉም

4 ተጫራቾች ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸዉ እና የወቅቱ ተጨማሪ እሴት ታክስ ሪፖርት የተደረገበት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል

5 ተጫራቾች የመቀርቡት ዋጋ ቫት ሳይጨምር መሆን ይኖርበታል (ነጠላ ዋጋ ከቫት በፊት ይቀመጥ)

6 ተጫራቾች ያሸነፋዎቸዉን እቃዎች በታዘዙበት ጊዜ ቢባዛ በ 7 ቀናት ዉስጥ ማስረከብ ግዴታ  ይኖርባቸዋል

7 በጨረታ ዋጋ ተንተርሰዉ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት ኣይኖረዉም

8 ተጫራቾች ዋጋቸዉን በታሸገ ኢንቨሎፕ ከ 11/04/2008 - 25/04/2008 ዓ/ም በስራ ቀን እና ሰዓት ኣክሱም ሆቴል ፊት ላፊት በሚገኘዉ ዋና ቢሮኣችን በመምጣት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ  የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ይኖርባቸዋል  በእያንዳንዱ የጨረታ እና የሰነዱ ማሸግያ ፖስታ የተጨራቾች ህጋዊ ማሀተም እና ፊርማ መኖር ይኖርበታል

9 የጨረታ ሳጥን ታህሳስ 25/04/2008 ዓ/ም ከቀኑ ልክ 8:00 ሰዓት የሚታሸገ ሲሆን ከዚሁ ሰዓት በኃላ የጨረታ ሰነድ ይዞ የሚመጣ ተጫራች ተቀባይነት ኣይኖረዉም

10 ተጫራችች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ልክ 8:30 ታህሳስ 25/2008 ዓ/ም በፋብሪካችን የግዢ እና ክምችት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 19 ዉስጥ ይከፈታል

11 ተጫራቾች በዚ ላይ ያሸነፋቸዉን የፅህፈት መሳሪያ ኣይነቶች ማሸነፋቸዉ እንደተነገራቸዉ በ  3 ቀናት ዉስጥ ዉል ይፈፅማሉ ይህ ሳይሆን ሲቀር ግን ተጫራቾች ያስያዘዉ የዉል መስከበሪያ ገንዘብ ካላ ምንም ቅደመ ሁኔታ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል

12 የyጨረታዉ ዝርዝር ሰነድ ከድርጅቱ ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 15 ድረስ በመምጣት እና የማይመለስ ብር 50 በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ

13 ማንኛዉ ተጫራች ጨረታ ከተከፈተ በኃላ ጨረታዉ መሰረዝ አይችልም
14 ስርዝ ድልዝ የዋጋ ማቅረቢያ ተቀባይነት ኣይኖረዉም

15 ፋብሪካዉ የተሻላ ኣማራጭ ካገኘ ማንኛዉም ጨረታዉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ

 

ስፖንሰሮች

ሃሳቦች የሚሰራጩባቸው መንገዶች.
Milkta Logo